ኢንስቲትዩቱ ከአለም ባንክ ጋራ የሚሰራቸዉን ፕሮጀክቶችን ለመተግበር የሚያስችል ንድፈ ሃሳብ እና የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ክለሳ እየተካሄደ ነው፡፡ የፕሮጀክቱን ንድፈ ሀሳብ እና የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ክለሳ የሚቀርጹት የኢንስቲትዩቱ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ናቸው፡፡

Federal TVET Institute

January 15, 2019

የኢንስቲትዩቱ የአካዳሚክ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር ባደረጉት ገለጻ ኢንስቲትዩቱ ከአለም ባንክ ጋራ የሚሰራቸዉ ፕሮጀክቶች ተፈፃሚ የመሆን እድላችው ከፍተኛ በመሆኑ የታለመላቸውን ዓላማ እንዲመቱ ለማድረግና ኢንስቲትዩቱን ወደ ቀዳሚ ተመራጭ ለማድረግ ሁሉም የጎላ አስተዋፅኦ ማድረግ አለበት ፡፡

ይህንን ለማሳካት ፕሮጀክቶችን ለመተግበር የሚያስችል ንድፈ ሃሳብ (term of reference) ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ በውስጡ ፤ለምን፤ እንዴት፡ የት፤ መቼ፤ እና ለማን እንደሚሰራ የሚገልፅ ሰነድ እየተሰራ ነው ፡፡

ባለሙያዎቹ ንድፈ ሀሳቡን ሲያዘጋጁ በተቋሙ እና በአለም ባንክ መካከል እንደ ውል የሚያገለግል ሲሆን እያንዳንዱ ተግባራት ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውን በግልጽ የሚያካትት ነው ፡፡

መግቢያ፣ አላማና ግብ፣የሃብት/የገንዘብ መጠን እና አጠቃቀም፣ ጥሮጀክቶቹ መቼ ተጀምረው መቼ እንደሚጠናቀቁ እንዲሁም ስራው ከተከናወነ በኋላ የሚጠበቁ ውጤቶችን የሚያጠቃልል ነው ብለዋል፡፡

በተያያዘም ንድፈ ሀሳቡ ፕሮጀክቱ እንዲተገበር እንደ እቅድ መሳሪያ ያገለግላል፡፡ በርካታ ፕሮጀክቶች በትክክል ባለመታቀዳቸው ምክንያት ወደ ፍፃሜ ሳይደርሱ እንሚዘገዩ ያስታወሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በተቋማችን ይህ አይነቱ ችግር እንዳይከሰት ከመጀመሪያ አንስቶ ግልፅ የሆነ የድርጊት መርሃ ግብር በማስቀመጥ ንድፈ ሃሳብ(term of reference በአጥጋቢ ሁኔታ መከናወን እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የአለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ቆዳና የቆዳ ዉጤቶች የልህቀት ማእከል ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ሳህለስላሴ ተካ በበኩላቸው ንድፈ ሀሳቡ ቀጥሎ ኢንስቲትዩቱን በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለማድረግ በማኑፋክቸሪክ ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ላይ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ክለሳ በመቅረጽ ይዘጋጃል ብለዋል፡፡

ከሁሉ በላይ ደግሞ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ላይ ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ተመጋግበውና ተደጋግፈው እንዲያድጉ የሚያደርገው የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን መሠረታዊ መርሁም በተፈለገው መልኩ ውጤታማ እንዲሆንም ያስችላል ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱን ንድፈ ሀሳብ እና የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ክለሳ የሚቀርጹት የኢንስቲትዩቱ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ባለሙያዎች በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ያጠቃልላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti