Human Resource Development Directorate

objectives 

500 በላይ ሠራተኞች ባለው ተቋም ውስጥ የሰው ሀብት አስተዳደር እና ልማት ዳይሬክቶሬት ሥራ በማቀድ፣ በመምራትና በማስተባበር፣ በመከታተልና በመገምገም የተቋሙን ተልዕኮና ዓላማ ሊያሳካ የሚችል ብቁና ጥራት ያለው የሰው ሀብት እንዲኖር ለማድረግ ነው ፡፡

ሥራው በተቋሙ የሰው ሀብት አስተዳደር እና ልማት ሥራዎችን ማቀድ፣ መምራት፣ ማስተባበርና መቆጣጠር፣ የስራ አፈጻጸም መገምገም፣ ክፍተቶችን መለየት፣ ማብቃት፣ ጥናቶች እንዲጠኑና መመሪያዎች እንዲከለሱ ማድረግ፣ የጥናት ውጤቶችን መገምገም፣ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ስምሪት ሥራዎች በደንብ እና በመመሪያ መሠረት እንዲተገበሩ ማድረግ፣ ተቋሙ ሜሪቲን የተከተለ የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ እንዲከናወን ማድረግ፣ የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ማድረግ፣ የመረጃዎችን ትክክለኝነት መረጃዎቹን በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ /በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ ተደራጅተው እንዲያዙ ማድረግ፤ የአጭርና የረጅም ጊዜ ትምህርትና ስልጠና በአግባቡ መጠቀም እንዲቻል የአፈፃፀም መመሪያ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤ በዕቅድ እና በጥናት ላይ የተደገፈ ስልጠና እንዲሰጥ ማስቻል እና የስልጠና ሂደቶችን መከታተልና መገምገም ተግባራት ማከናወን::