Objectives
1.በተቋሙ ውስጥ የትውልድ ሥነ-ምግባርና የሞራል እሴቶችን በብቃት መገንባት፣
2. የሙስና ወንጀልን እና ብልሹ አሠራርን መከላከል፣
3. የሙስና ወንጀል ተፈፅሞ ከተገኘ ለሚመለከተው አካል ጉዳዩን ማቅረብ
4. በተቋሙ ውስጥ ሚገኙ የመንግሥት ተሿሚዎች እና ሠራተኞች ሀብትና የገቢ ምንጮቻቸውን በማሳወቅ፣በመመዝገብ፣ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ እና የተጠያቂነት ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ ነው፡፡
በተቋሙ የሚሾሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የሥነ-ምግባር እና የሙስና መከላከል ስልጠና ኢንዲወስዱ ማድረግ፣በተቋሙ ወስጥ ለሙስና እና ብልሹ አሠራር የተጋለጡ እና ሊጋለጡ የሚችሉ የአሠራር ሥርዓቶችን በማጥናት የመፍትሔ ሀሳቦችን ማቅረብ፣ተግባራዊ መሆናቸውን መከታተል፣ በማይፈፀሙት ላይ ተገቢ የሆነ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በህግ የመመርመርና የመክሰስ ስልጣን ላለው አካል ማቅረብ፣ ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ሲጠረጠር ወይም ለመከታተያ ክፍሉ ጥቆማ ሲደርስ ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስቸኳይ ሙስና የመከላከል ሥራ በመሥራት ሂደቱ እንዲቋረጥ ወይም አስፈላጊው ማስተካከያ እንዲደረግ ለበላይ ኃላፊ የውሣኔ ሀሳብ ማቅረብ፡፡ የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያሳውቁ እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፤መረጃውም በአግባቡ ተደራጅቶ እንዲያዝ ማድረግ፡፡ የጥቅም ግጭትን የመከላከል፡፡ የተቋሙን የሠራተኞች የሥነ-ምግባር ደንብ ማዘጋጀት፤ማስፀደቅና ሥራ ላይ መዋሉን መከታተል፡፡ በተቋሙ ውስጥ የፀረ-ሙስና ህጎች መከበራቸውን ማረጋገጥ፤ስለአፈፃፀማቸው ለበላይ ኃላፊ የምክር አገልግሎት መስጠት፣የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ዓመታዊ የዓለም የፀረ-ሙስና ቀን እንዲከበር ማድረግ፣ በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያ መልካም ሥነ-ምግባርን ለመገንባት የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማስተላለፍ፣የስልጠና ክፍተት በመለየት ለሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በየጊዜዉ የመልካም ሥነ-ምግባርና በሞራል እሴት ዙሪያ በተለያዩ ርእሶች ስልጠና መስጠት፣ በብልሹ አሠራር ዙሪያ ከተቋሙ ሠራተኞችና ተገልጋዮች ጥቆማ መቀበልና ተገቢነቱን በማየት አጣርቶ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣