ስልጠናው የኢንስቲትዩቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ያግዛል ተባለ፡፡

Federal TVET Institute

November 1, 2019

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኢንስቲትዩቱ ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ ግብኣቶችን የማቅረብ ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት ክፍል ነው፡፡

የተማሪዎችን የምግብ እና ምግብ ነክ ግብአቶችን የማሟላት ስራ ይሰራል፤ የትምህርት መሳሪያዎችን የማሟላት፣ ለተማሪዎች ፕሮጀክት መስሪያ ግብኣቶችን የማቅረብ፣ እንዲሁም የተቋሙን የግንባታ ፕሮጀክቶች የማስፈጸም ስራ ይሰራል በተጨማሪም ለሰራተኞች የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ያሟላል፡፡

በዚህም ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ቢገኝም የግዥ ስርዓቱ ቀልጣፋ እንዳይሆን እንቅፋቶች ሲገጥሙት ቆይተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል የፋይናንስ ስርዓቱን አለመገንዘብ ዋነኛው እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡
ከየስራ ክፍሎች የሚቀርቡ የግዢ መጠየቂያዎች መግለጫቸው /specification/ ገላጭ አለመሆን፣በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ ደውሎድ በማድረግ ሳይታረም ማቅርበ ፣የሚቀርበው ግምታዊ ዋጋም የተጋነነ ወይም በከፍተኛ ሁኔታ የወረደ መሆኑ እንዲሁም ወቅቱን ያልጠበቀ ጊዜው ያለፈበትን የግዢ ፍላጎት ማቅርብ ብሎም ያለማቅረብ በዚህ የተነሳ የግዢ መጓተት ያስከተለ መሆኑ እንደ ችግር ይጠቀሳሉ፡፡

ኢንስቲትዩቱ እነዚህንና መሰል ተያያዥ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል የአቅም መገንቢያ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት በሁለት ዙሮች በአዳማ ከተማ እየሰጠ ይገኛል፡፡

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደምሰው በየነ ስልጠናውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ‹‹ስልጠናው የእቅድ አስተቃቀድን ጨምሮ የግዥ ሥርዓት እና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር ነው››
‹‹ባለሙያዎች እና አመራሮች ግንዛቤ ቢፈጠርላቸው ለውጥ ያመጣል በሚል ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎበት ነው ስልጠናው እየተሰጠ የሚገኘው›› ብለዋል፡፡
ስልጠናውን ከኢንስቲትዩቱ ልምድ ካላቸው ከፍተኛ ባለሙያዎች በተጨማሪ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች እንዲሁም ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ባለሙያዎች ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎበት ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በመጨረሻም አቶ ደምሰው ‹‹ይህ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲጠናቀቅ በግዥ ጥያቄ አቀራረብ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል፤ ይህ ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጣችንን በማቀላጠፍ ውጤታማ የመማር ማስተማር ስራ ለመስራት ያግዘናል›› ብለዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti