International Research and Development Seminar and Technology Competition to be Held in Addis Ababa. June 03/2018.

International Research and Development Seminar and Technology Competition to be Held in Addis Ababa.
***June 03/2018 ****
The Ethiopian Technical and Vocational Training Institute will hold a competition and conference in Addis Ababa, where research and development and technology innovation experts from 16 different countries will participate.
The Deputy Director General of the Institute’s Research and Development Community Service, Habtamu Mulugeta (PhD), gave a statement to journalists regarding the event.
According to the Deputy Director General, the event will be opened at the Adwa Victory Memorial Museum on Friday, June 5/2018, with a grand ceremony attended by researchers, technology innovation experts, industry owners, ambassadors, senior government officials and other invited guests.
It is said that Ethiopia will gain valuable experience and expertise in its efforts to strengthen skills development and technology innovation in the coming era.
The event will be held from June 5- June 7/2018.
ዓለምአቀፍ የጥናትና ምርምር ሴሚናር እና የቴክኖሎጂ ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
***ሰኔ 03/2018 ዓ.ም ****
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተለያዩ 16 አገራት የጥናትና ምርምር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ውድድርና ጉባኤ በአዲስ አበባ ያካሂዳል።
ሁነቱን አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ(ዶ/ር) ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
እንደምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ሁነቱ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተመራማሪዎች፣ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለሙያዎች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት አርብ ሰኔ 5/2018 ይከፈታል።
ሁነቱ ላይ ኢትዮጵያ መጪውን ዘመን ያለመ የክህሎት ልማት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ለማጽናት ለምታደርገው እንቅስቃሴ ጠቃሚ ልምድና ተሞክሮ ታገኛለች ተብሏል።
ኹነቱ ከሰኔ 5- ሰኔ 7/2018 ይካሄዳል።