የኢንደስትሪ ሙያተኞች ብቁ የሚሆኑበትን ዓለምአቀፍ ተቀባይነት

የኢንደስትሪ ሙያተኞች ብቁ የሚሆኑበትን ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ክህሎት እያስጨበጠ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ #የብየዳ_ስልጠና_እና_ቴክኖሎጂ_ማዕከል አስታወቀ።

***************

የብየዳ ቴክኖሎጂ በተለያዩ የስራ አይነቶች ላይ የሚፈለግ ውድ ሙያ ነው። ከንፋስ፣ ከጸሐይ፣ ከውሐ ሐይል ማመንጫዎችን እና ሌሎችንም ትልልቅ ፕሮጀክቶች ለመገንባት፣ የነዳጅ ጫኝ መኪኖችን ለመበየድ፣ ግዙፍ ሠማይ ጠቀስ ሕንጻዎችን ለመገንባት የብየዳ ቴክኖሎጂ የግድ የሚያስፈልግ ክህሎት ነው።
ለዚህም ከተለምዷዊ አሰራር የወጣ ዘመናዊ እና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተመዝኖ ተቀባይነት ያገኘ ስልጠና የወሰዱ ሙያተኞች ያስፈልጋሉ።

አቶ #ፋንታሁን_የማነ የስልጠና ማዕከሉ ተወካይ ሀላፊ እና የብየዳ ስልጠናና ሠርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው።

በአገራችን የሚገኙ የብየዳ ሙያተኞች በሚሰሯቸው ስራዎች እና ባላቸው ክህሎት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። ያልሰለጠኑ ወይም ከሰለጠኑበት ደረጃ በላይ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሰሩ አሉ። ይህንን በጥናት የለየው ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የብየዳ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ብቁ የብየዳ ሙያተኞችን ለማፍራት እየተጋ ሲሆን እንደ አገር ያለብንን አለምአቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ሙያተኞች እና ተቋማት ክፍተቶች ለመሙላት እየሠራ ነው ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ ደረጃውን የጠበቀ የስልጠና ማዕከላትን በማደራጀት፣ ብቁ ሙያተኞችን በመመደብ፣ አስፈላጊውን የፍተሸ ላብራቶሪ በማሟላት፣ የስልጠና፣ የምዘና እና የአጣሪ ቡድን በማቋቋም ብቁ ተቋም ሆኖ በመገኘቱ ከዓለምአቀፍ የብየዳ ኢንስቲትዩት (IIW) የማሰልጠንና ስተፊኬት የመስጠት ሙሉ እውቅና አግኝቷል።
ስልጠናውን በስፋት ለማስቀጠል ሠፊ ንቅናቄ መጀመሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ #የሥራና_ክህሎት_ሚኒስቴር ከ #ሜድሮክ_ኢንቨስትመንት_ግሩፕ ጋር በክህሎት ልማት ላይ በጋራ ለመስራት በፈጠሩት ስምምነት ከተለያዩ ካምፓኒዎች ለተውጣጡ ሙያተኞች አለም አቀፍ ደረጃ ባላቸው በአራት የብየዳ አይነቶች ማለትም

– Manual Metal Arc (MMA) Welding,
– Metal Active Gas (MAG)/Metal Inert Gas (MIG) Welding,
– Tungsten Inert Gas (TIG) Welding
– Oxy-acetylene welding የሞጁል አንድ ስልጠና (Basic) መስጠት ተጀሞሯል። በቀጣይም በተካታታነት እስከ ሞጁል ስድስት ይቀጥላል ብለዋል።

ስልጠናውን ሲወስዱ ያገኘናቸው #መለሰ_መርዕድ ከሆራይዘን አዲስ ጎማ እና #ይስማሸዋ_ደረሰ ከኮምብልቻ ብረታ ብረት በብየዳ ሙያ ከሦስት እና ከአስር ዓመት በላይ ልምድ እንዳላቸው ነገር ግን እንደዚህ አይነት ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና ያልወሰዱ በመሆኑ ብዙ መስራት ሲችሉ ያንን እንዳላደረጉ በቁጭት ገልጸውልናል። ከዚህ በኋላ ግን ራሳቸውንም ተቋማቸውንም ውጤታማ የሚያደርጉበት ክህሎት መጨበጣቸውን ተናግረዋል።

በስልጠና አሠጣጡ ደስተኞች መሆናቸውንና ተመሳሳይ ስልጠናዎች በዘርፉ ላሉ ሙያተኞች ሁሉ ቢደርስ እንደአገር ትልቅ ለውጥ እንደሚመጣ እምነታቸውን ገልጸዋል።