Welcome to FDRE Technical and Vocational Education and Training Institute
Deputy Director General for Technology and Enterprise Development
Deputy Director General for Technology and Enterprise Development
ስልጠናችን ከዳቦ በላይ ሆኖ ገቢ የሚያስገኝ ሆኖ እንድሆን ያለተቆጠበ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ እየተሰጠ ያለ ስልጠና ከራስ ጉርስ አልፎ ለሌላውም መተዳደሪያ ወይም የገቢ ምንጭ መሆን አለበት የተባለው አዲሱ ዕሳቤ
የኢንስቲትዩታችንና የለየሎችንም ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን የመጡበትን መንገድ ቆም ብለው እንድፈትሹ የሚያስገድድ ነው፡፡ ኢንስቲትዩታችን የተቋማችን ማህበረሰብ በመጀመሪያ በማነቃነቅ፣ በተጨማሪም ሌሎች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ችሎታ ያላቸውን ዜጎች በመጠቀም በአገራችን ባሉት የመንግስት ተቋማት ያላተለመዱ ስራዎች መስራት የሚያስችል እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል፡፡ ዕውቄቶችና እና ችሎታዎች በሚሰናሰሉበት ጊዜ የተሻለና ተለቅ ያለ ነገር ለመስራት ወይም ችግር ፈቺ የሆነ ነገር ለመፍጠር ያስችላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ቴክኖሎጂዎችን ሁልጊዜ ከውጭ ገዝቶ ከመጠቀም ተላቅቀን አንዳንዶችን አገርቤት ለማምረት ሌሎችን ደግሞ ለእኛ በሚስማማ መልኩ አሻሽሎ ለመስራት እንቅስቃሴዎች የተጀመሩ በመሆናቸው ተበታትነው ያሉትን ችሎታዎችን በማሰባሰብ ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን ወደማፍለቅ እየገባን ነው፡፡
ትልቅ ነገር መስራት ትልቅ ትዕግስት እንዲሁም ትልቅ ትብብር ይፈልጋል፡፡ አንዱ ያለውን ችሎታና ክህል ከሌላው ጋር በምያጣምርበት ጊዜ አንድ የተሻለ ነገርን ለማምጣት ወይም ለመፍጠር ያግዛል፡፡ በመሆኑም በጥምረት የሚፈልቁ ችግር የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎችን እንደአገር በማውጣት፣ የወጣውንም በትብብር ወደምርት በማስገባት ያብንን ችግሮች ለማቅለል እየተሰራ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግርና እንተርፕራይዝ ልማት ስራ ዘርፍም ይህንን እሳቤ በመላው አገሪቱ በማስፋት የሚመጣውን መልካም ውጤት ለማየት ተግቶ እየሰራ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንግስት ተቋማት ትብብር ብቻ ሳይሆን የግሉ ዘርፍ አማራቾች፣ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦች፣ የፈጠራ ልምድና ክህሎት የያዙ ዜጎች፣ ባላሀብቶችና አምራቾች ወዘተ መጣመርከመቸውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ትልቅ ነገር ለመስራት በተጀመረው ትብብር ውስጥ ሁላችሁም አሻራችሁን በመተው ብልጽግናችን ለማረጋገጥ በምናደረገው ትግል አብሮአችን እንዲትሆኑ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡