Message From The Deputy Director General for Administration
የኢፌዲሪ ቴክንክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን የቴክንክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍን ብቁ
ለማድረግና ለአገራዊ የልማት ስራዎች በቂና የበቁ ሙያተኞችን ለማፍለቅ እየሰጠ ላለው የአጫጭርና የረጅም
ስልጠናዎች ስከት የአስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክር አስፈላጊውን ሁሉ ያሟላል፡፡ ፈጣንና አርኪ ምላሽ የሚሠጡ ባለሙያዎችን ከማሟላት ባሻገር የስልጠና፣ የቴክኖሎጂ እንዲሁም የጥናትና ምርምር፣ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች ግባቸውን እንዲመቱ የሚያግዙ ግብዓቶችን ያመቻቻል፡፡
የቴክንክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የተሻለ ሙያዊ ክህሎት ያላቸው ስልጣኞችን ለማብቃት ከሌሎች የትምህርትና
ስልጠና ስራዎች አንጻር ከፍ ያለ ወጪ ይጠይቃል፡፡ ይህ ማለት ስልጠናው የሚፈልገው አሰልጣኝም፣ አመራርም ሆነ መሰረተልማት የራሱ የሆነ ባህሪ ያለው መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ኢንስቲትዩታችን የኢትዮጵያ መንግስት ከሚሰራቸው የስልጠናና የኑሮ መሰረተልማቶች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህዝብ የልማት አጋር ከሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ባገኘው ዕገዛ የተዋጣ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል ቁመና የተላበሰ ነው፡፡
ያሉንንም ውድ የስልጠና መሰረተ ልማቶች ከሌሎች ከፍተኛ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር እየተጋራን ሲሆን በበይልጥ ለማስፋት የተጀመሩ ስራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና ቴክኖሎጂ አፍላቂዎች ተረጋግተው ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያችላቸውን መሰረተ ልማቶችን ማሟላትና ማሻሻል የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በዚህም የተጀመሩ የግንባታ፣ የጥገና ፕሮጀክቶችንና ሌሎች የተቋሙንና ሰፊውን መህበረሰብ የሚጠቅሙ መሰረተልማቶችን እያሰፋን እንሄዳለን፡፡
የአሰልጣኖችና የኢንዱስትሪ ቴክኒሻኖችን አቅም በስፋት ለመገንባት ያሉንን አማራጮችን አሟጠን ለመጠቀም
ከዋናው ግቢ ባሻገር ያሉትን አማራጮችንም በሚገባ ለማየት እንገደዳለን፡፡ ስራዎቻችን ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ መከታተል ብቻ ሳይሆን ወጪ ቆጣቢ እንዲሆኑ የህዝብና መንግስትን ሀብትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እያዋልን የተጣለብንን አገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሚናደርገው ርብርብ መላው ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲንትቆሙ ጥሪየን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡