ኢንስቲትዩቱ በልደታ ክ/ከተማ ለሚኖሩና በከፍተኛ ደረጃ ለችግር ለተጋለጡ እንደዚሁም ዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋይ ለሆኑ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

Federal TVET Institute

04 Aug 2020

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይክተር  አቶ ተሸለ በሬቻ እንደተናገሩት፤ የኢንስቲትዩቱ  የማህበረሰብ አገልግሎ በተለይም ኮሮና ወረርሽን እየተባባሰ ከመጣበት  ጊዜ ጀምሮ  ይበልጥ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን እየረዳ እንደሚገኝ  ገልጸዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችለውን ቀውስ  እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባይሆንም ተደጋግፎ ይህን ክፉ ጊዜ ማለፍ እንደሚቻል ለማሳየት ነዉ ብለዋል ፡፡

ኢንስቲዩቱ እና መምህራኖች በጋራ በልደታ ክ/ከተማ  ለሚኖሩ   ከዚህ ቀደም ድጋፍ አግኝተው ለማያውቁ እጅግ አሳዛኝ በሆነ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እና  የኢንስትዩቱ ዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋይ ለሆኑ 60 ሰራተኞች የተሰጠ መሆኑ ነው ብለዋል።

ሀገር አቀፍ  የኮቪድ-19 መከላከል ንቅናቄ እና ምርመራ ዘመቻ በመቀላቀል  የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችንና   ድጋፎችን ማከናወኑን እና በዚህም የቫይረሱን ስርጭት መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ የበኩሉን ድርሻ ኢንስቲትዩቱ ይወጣል ብለዋል አቶ  ተሻለ። 

ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የጥናትና ምርምር የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ እንየው  ጌትነት   በበኩላቸው  እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተደራሽነት በጣም አስቸጋሪ የሆኑና ብዙውን ጊዜ በመንግሥትና በተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሚደረጉ ድጋፎች ሳይታዩ የቆዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

 እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች በበጎ ፈቃደኞች በማስጠናት ችግረኝነታቸው ከሚኖሩበት ቀበሌ እንዲረጋገጥ በማድረግ ለተመረጡ  ግለሰቦች በነፍስ ወከፍ ቢያንስ ለአንድ ወር የሚበቃ ፍርኖ ዱቄት፣ ፓስታ፣ መኮሮኒ፣ ዘይት፣ ሳሙና፣ ፊት መሸፈኛ ጭንብልና የእጅ ንጽህና መጠበቂያ (ሳኒታይዘር) አከፋፍሏል ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ  የወገን አለኝታ በመሆን  በመዲናችን  ውስጥ በኮረና ወረርሽኝ ምክኒያት ከፍተኛ ተጠቂዎች ያሉባት ለልደታ ክፍለ ከተማ ለተደረገላቸው ድጋፍ የክ/ከተማዉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኢሳያስ ምህረት አመስግነዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti