በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የክህሎት፤ ቴክኖሎጅና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዉድድር፤ ሲምፖዚየምና አውደ ርእይ ክንውን እና የ2ኛ ዙር እቅድ ቀርቦ ምክክር ተደርጓል፡፡ የክልሎች የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሀላፊዎች፣ የፖሊ ቴክኒክ አመራሮች፣የሳተላይት ሀላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

Federal TVET Institute

November 10, 2019

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጣና ኢንስቲትዩቱ እና ኤጀንሲው የመጀመሪያ በነበረዉ የክህሎት፤ ቴክኖሎጅና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዉድድር፤ ሲምፖዚየምና አውደ ርእይ ላይ የነበሩ ጥናካሬዊችና ክፍተቶችን የተካተቱበት ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጣና ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክቶ አቶ ሀብታሙ ክብረት ሲሆኑ አውደ ርእዩ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት እያበረከተ ያለዉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለህዝብ ያስቃኘንበት ፣ለህዝብ በማስተዋወቅና እንዲሁም በተቋም፤ በክላስተር፤ በክልልና በአገር አቀፍ ደረጃ በማካሄድ ቴክኖሎጅስቶች፤ የክህሎት ባለቤቶችና ተመራማሪዎች ከህዝብ ጋር እንዲተዋወቁና እንድበረታቱ የተደረገበት ነበር ብለዋል፡፡

የኢንተርፕራይዞችን የስራ እድል ፈጠራን ለማበረታታት ምርትና አገልግሎታቸዉን ለህዝብ እንዲተዋወቁ የተመቻቸ ሁኔታ በመፍጠር፣የአጋር አካሎችን ድጋፍ በማሳደግ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሞክሮ የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉ በጥንካሬ ከተከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡

እንደ ክፍተት ከተጠቀሱ ስራዎች ዋና ዋናዎች ለዉድድሩ ተሳታፊዋች፤ ለዳኞች እና ለዝግጅቱ ላይ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስክር ወረቀት ለሁሉም ተደራሽ አለመሆን፣ የበጀት ፣የግብአት እጥረት፣የኮሚቴዎች በደራሽ ስራዎች መጠመድ፣ሁነቱን በተመለከተ መረጃ የሚሰጡ ህትመቶች አለመዘጋጀታቸው ፣ተጠቅሰዋል፡፡
የኤጀንሲዉ ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪ አምላኩ አለባቸው 2012 መሪ እቅድ ቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎች የነበሩ ክፍተቶችን እና በእቅድ ላይ መካተት አለባቸው ያሉትን የተለያዩ ሀሳቦችጠቅሰዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ እንየው ጌትነት እና ኤጀንሲው ም/ዋና ዳሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በዘንድሮ አመት ለሚከናወነዉ የ2ኛዉ ዙር ዉድድር፣ ኤግዚቭሽንና ስምፖዚየም ከተገኘዉ ተሞክሮ በመነሳት የተሻሉ ተወዳዳሪዎችን በመቅረብ አለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ብቁና ጠንካራ ተወዳዳሪዎችን ማቀረብ በተለይ ከክልሎች እንደሚጠበቅ የተናገሩት አቶ ተሻሌ በሬቻ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጣና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ናቸዉ፡፡

በመጨረሻም ለእያንዳንዱ ዉድድር በቀረበዉ መስፈርት ተሳታፊዎች ሀሳብ አቅርበዉ በመስማማት ወደ ስራቸዉ ተመልሰዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti