ኢንስቲትዩቱን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሳደግ አዲስ ማቋቋሚያ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተልኳል ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የ2012 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ ክንውኑን ገምግሟል፡

Federal TVET Institute

October 31, 2019

የ2012 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት ያቀረቡት የኢንስትቲቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ክፍሌ ሲሆኑ ኢንስቲትዩቱን ወደ ዩንቨርስቲ ለማሳደግ በሚያደርገው ጉዞ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ አዲስ ማቋቋሚያ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ገልጸዋል፡፡ ደንቡ በህደትም በምንስትሮች ምክር ቤት ምክክር ይደረግበታል፡፡

ለዚህም በቴክኖሎጂው ዘርፍ በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ካላቸው ዩንቨርስቲዎች ልምዶችን ለመቅሰም መምህራን በሁለት ቡድን ተከፋፍለው ወደ ጋና እና ሲንጋፖር ከሚገኙ ቴክኒካል ዩንቨርስቲዎች አሰራርና አተገባበር ልምድ ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ12ተኛ ክፍል ያጠናቀቁ የዘመኑ የከፍተኛ ትምህርት ውጤት መቁረጫ ነጥብ ያላቸው ተማሪዎችን በዲግሪ መርሀ ግብር ለማስተማር መቀበሉን ተከትሎ የመግብያ ፈተና/Entrance Exam በሁሉም የትምህርት ክፍሎች እንዲሰጥ ተደርጓል የኮመን ኮርስ መምህራን ቅጥር እንዲፈጸም መደረጉ በሩብ አመቱ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው ፡፡

በተያያዘም ኢንስትቲዩቱ ለመጀመሪያ ዲግሪ እና ለሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር ስርአተ ትምህርቶችን በአዲስ መልክ የማዘጋጀት እና የመከለስ ስራ መሰራቱ፤ የ2011 ዓ.ም ሰልጣኞች ምረቃ በደማቅ ሁኔታ መከበሩ፣ በተመራቂ ተማሪዎች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን በመለየት ፋብሪኬሽን ዉስጥ በሚሰሩ ባለሙያዎች በጥራት ተሰርቶ እንዲሸጋገር ለማድረግ የመለየት ስራ መሰራቱ፣ ከ1200 በላይ ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራ ስራ መሰራቱ ተጠቅሷል፡፡

ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ሴት ተማሪዎችን ለማበረታታት 24 ሰዓት የኢንተርኔት አገልግሎት በመኝታ ቤታቸዉ አካባቢ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ፤ ለነፍሰ ጡር እና አካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች መሬት (ግራውንድ) ላይ የመኝታ ክፍል እንዲያገኙ በማድረግ አስፈላጊዉ ድጋፍና ክትትል የማድረገ ስራ ተሰርቷል፣

በመድረኩም፣ የመማር ማስተማር የምርምር ስራ በአይሲቲ ለመደገፍ፣ የአይሲቲ መሰረተ ልማቶች በታቀደዉና በሚፈለገዉ ልክ እየተሟላ አለመሆኑ፣ የዕቅድና የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በጥራትና ወቅቱን ጠብቆ አለማቅረብ፣ ከኢፍሚስ ጋር በተገናኘ የኔትዎርክ ችግር መኖሩ የተሽከርካሪ እጥረት መኖር፣ የለውጥ ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ አለመፈጸም፣ ለተማሪዎች የአምቡላንስ መኪና አገልግሎት አለመኖር፣ የመማሪያ ክፍሎች ላይ የካይዘን አተገባበር እና የቢሮ ጥበት እና መሰል እጥረቶች እንደተስተዋሉ ተነስቷል፡፡

በእለቱ በመድረኩ ላይ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በሬቻ ተገኝተው በቀጣይ መምህራንም ሆነ አስተዳደር ሰራተኞች በዩንቨርስቲ ደረጃ በሚመጥን መልኩ በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ ፣ በእውቀትና ፣በክህሎት ራሳቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

መምህራኖች ተማሪዎችን አደረጃጀት (quality circle )የግንኙነት ጊዜ በማስቀመጥ ቡድኑ የማጠናከር ስራ መስራት ፣የተቋሙ መሬት ይዞታ የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል፣ የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ግንባታ መጠናቀቅና ማስረከብ፣ በዋና ግቢ እና የምህንደስና ልህቀት ማአከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ግንባታ ስራ ማስጀመር፣ የድህረ ምረቃ የተማሪ ፕሮጀክቶች የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ ትኩረት ማድረገቸውን ማረጋገጥ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ናቸው ብለዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti