ኢንስቲትዩቱ የወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።

ኢንስቲትዩቱ የወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።
********ነሀሴ 22/2018******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጨፋሮ ቢት ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የቁሳቁስ ድጋፍ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር፣ ኢንስቲትዩቱ የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተጋ መሆኑን ገልጸዋል።
ወጣቶች ክህሎት ይዘው በራሳቸው ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚሠራው ኢንስቲትዩቱ በየጊዜው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሠጠ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው አንስተዋል።
በእለቱ ኢንስቲትዩቱ ያመረታቸው የተሻሻሉ የተገጣጣሚ ጡብ ማምረቻ 15 ማሽኖች ለወጣቶች ርክክብ ተደርጓል። የማሽኖች ዋጋም 3ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ “ቴክኖሎጂ፣ ወጣትነት፣ የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብና ፈጠራ” በሚል ርዕስ ለ300 ወጣቶች ስልጠና ተሰጥቷል።
የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰይድ መሃመድ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ለወጣቶች ተጠቃሚነት የጀመረውን ሥራ አድንቀው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
አስተማሪና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ማማየ አደላ እና የስኪል ኢትዮጵያ ፕሮግራም የቴክኖሎጂ ባለሙያው ወጣት ቶማስ ብርቅህ ለወጣቶቹ ስልጠና ሰጥተዋል።