Advancing Agriculture and Agro-processing through TVT for sustainable, digital and climate-resilient future.
የግብርና ዘርፍን ለማዘመን የቴክኒክና ሙያ ሚና ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የጥናትና ምርምር ስራዎች
**ግንቦት 12/2018******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ 2ኛው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ Advancing Agriculture and Agro-processing through TVT for sustainable, digital and climate-resilient future. በሚል መሪ መልዕክት አዘጋጅቷል፡፡
የኢንስቲቲዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ሴሚናሩን ሲከፍቱ እንደገለጹት የግብርናና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ላይ ጥናት ማጥናት፣ መመካከር፣ ለችግሮች መፍትሄ ማበጀት ወቅቱ የሚይቀው ቁልፍ ጉዳይ በሆነበት ጊዜ የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል፡፡
ይህ ኮንፈረንስ ለአጥኚዎች፣ ለተመራማሪዎች፣ ለአሰልጣኞችና ሰልጣኞች በግብርናው መስክ አዲስ ነገር እንዲያፈልቁ፣ የዘርፉን ችግሮች ነቅሰው እንዲለዩ እና ለመፍትሄው እንዲመክሩ የሚያስችል መድረክ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።
ዶ/ር ሀብታሙ፣ ግብርና የኢኮኖሚያችን ምሰሶ እና የሚሊዮኖች ዜጎች የኑሮ መሰረት የሆነ ዘርፍ በመሆኑ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማሳደግ፣ በምርምር ለመደገፍ የተመራማሪዎች፣ የቴክሎጂስቶችን ሚና የሚጠይቅ ኦንደሆነ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በጥናትና ምርምር ካመጣቸው ለውጦች መካከል በየሳምንቱ ከሚካሄዱት ሴሚናሮች ባሻገር በፋካሊቲዎች የሚዘጋጁት ዓመታዊ ኮንፈረንሶች ይገኙበታል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ የመጀመሪውን ዓለምአቀፍ ኮንፈረንስ ለማዘጋጀትም ዝግጅቱ መጠናቀቁን አንስተዋል፤፤
የኢንስቲትዩቱ የአግሮፕሮሰሲንግ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ዲን ዶ/ር ሳምራዊት ሙሉጌታ ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ባህሉ በፋካሊቲው በሚሰሩ ስራዎች ላይ ትልቅ ፋይዳ እያበረከተ መሆን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መድረክ በርካታ ዘርፉን የሚለውጡ የጥናት ስራዎች መቅረባቸውን ገልፀው ተጨማሪ ግብአት የሚጠምሩ ውይይቶች እንደሚካሄዱባቸው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ሳምራዊት፣ ኢንስቲትዩቱ ፋካሊቲዎች በየዓመቱ ሴሚናር ማካሄዳቸው በየዘርፎቹ ምሁራን እንዲመክሩ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቁልፍ መልዕክት ለማስተላለፍ የተገኙት ዶ/ር አሻግሬ ዘውዱ Modernizing of indigenous food foods በሚል ያዘጋጁትን ጽሁፍ አቅረብዋል፡፡
ዶ/ር አሻግሬ በመልዕክታቸው አገር በቀል ምግቦች አንድም በንጥረነገር የዳበሩ በመሆናቸው፣ አንድም በባህል ተቀባይነት ያላቸው በመሆኑ እንዲሁም አየርንብረትን የሚጠብቁ (climate resilient) በመሆናቸው ትኩረት አድርገን ልንሠራባቸው ይገባል ብለዋል።
ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት አገርበቀል የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል ወሳኝ ተቋማት መሆናቸውን የገለጹት አቅራቢው ሥርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር ቁልፍ ተቋማት ናቸው ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ቴክኒክናሙያ ስልጠና ተቋማት ዜጎች በምግብ ኢንተርፕረነር እንዲሆኑ በወርፉ ላይ ተሠማርተው እንዲሠሩ ማገዝ እንደሚገባቸው አንስተዋል።
በጽሁፋቸው በተለይም ጤፍንና ቆጮን መነሻ አድርገው በዘርፉ ሊሰሩ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ተናግረዋል።
በመድረኩ 7 የጥናትና ምርምር ስራዎች ቀርበው ሠፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/@fdretvtistitute
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R









