ኢንስቲትዩቱ ከ “ዳን ቴክኖክራፍት” ጋር መስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ የኢንደስትሪ ጉብኝት ተካሄደ።

ኢንስቲትዩቱ ከ “ዳን ቴክኖክራፍት” ጋር መስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ የኢንደስትሪ ጉብኝት ተካሄደ።
***********መጋቢት 10/2017*****
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከዳን ቴክኖክራፍት ሀ/የተ/የግል ኩባንያ ጋር በቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ስራዎች አብሮ ለመስራት የሚያስችል የኢንደስትሪ ጉብኝት ተካሂዷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እና የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ የ”ዳንሊፍት” ማምረቻ ፋብሪካዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በትብብሩ ዙሪያ ከአቶ ዳንኤል መብራህቱ ጋር መክረዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ተቋማቱ በበርካታ መስኮች አብረው የሚሰሩባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን አንስተዋል።
ኢንስቲትዩቱ እንደ “ክህሎት ኢትዮጵያ” ባሉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት እንዲፈጠሩ በሚሰራባቸው ፕሮግራሞች አማካይነት ተኪ የፈጠራ ውጤቶችን በማምረት በስፋት ለገበያው ማቅረብ አንዱ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
የካምፓኒውን የበርካታ ዓመታት የዳበረ ልምድ እና የኢንስቲትዩቱን ዘመናዊ ወርክሾፖች በማቀናጀት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻልም ጨምረው ተናግረዋል።
ካምፓኒው ለኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች የኢንደስትሪ ልምምድ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ይሠራል የሉ ሲሆን፣ በጥቅሉ የክህሎት ልማቱ ላይ በትብብር ለውጥ ለማምጣት መስራት ይገባልም ብለዋል።
ላለፉት 52 ዓመታት በአገራችን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደ ገበያ እያቀረበ የሚገኘው ዳን ቴክኖክራፍት ይበልጥ በ”ዳን ሊፍት” ስሙ ጎሎቶ የሚታወቅ አገር በቀል ካምፓኒ መሆኑን የገለጹት የድርጅቱ ባለቤትና ሀላፊ ኢንጂነር ዳንኤል መብራህቱ ናቸው።
በዚህም ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቴክኖሎጂና ፈጠራ መስክ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።