በኢንስቲትዩታችን ደረጃ 7 (2ኛ ዲግሪ) ለመቀጠል ለተመዘገባችሁ፣ ማመልከቻ ላስገባችሁ በሙሉ። ***********************************

በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ደረጃ 7 (2ኛ ዲግሪ) ለመቀጠል ለተመዘገባችሁ፣ ማለትም
ከየክልሎቻችሁ ተመልምላችሁ የተላካችሁ፤ ከ 12ኛ ክፍል አልፋችሁ በኢንስቲትዩታችን የመጀመሪያ ዲግሪ የያዛችሁና በኢንስቲትዩቱ (ደረጃ 7 ሁለተኛ ዲግሪ) ለመቀጠል ማመልከቻ ያስገባችሁ በሙሉ
ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ እንደ መስፈርት ተቀምጧል። በመሆኑም አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያሊንክ በኩል ይከናወናል፡፡
ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።
.
የመፈተኛ ‘ USER NAME ‘ እና ” PASSWORD ‘ በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል፡፡
.
ማሳሰቢያ
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ ሆኖ በፈተና ወቅት የተሰጣችሁን User Name and Password፣ እና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቃባችኋል።