የ21ኛው ክ/ዘመን ት/ቤት ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ ከድር ገለጹ።

የ21ኛው ክ/ዘመን ት/ቤት ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ ከድር ገለጹ።
**************የካቲት 18/2017********
በክህሎት እና በፈጠራ የበቁ ዜጎችን ለማፍራት እየሰራ የሚገኘው የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የመጀመሪያ የሆነውን የ21ኛው ክ/ዘመን ት/ቤት እየገነባ ይገኛል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የት/ቤቱን ግንባታ ሂደት በአካል ተመልክተው የደረሰበትን ደረጃ ገምግመዋል።
በኢንስቲትዩቱ፣ በኮንትራክተሩ፣ እና በአማካሪ ድርጅቱ መካከል በተካሄደው በዚህ የሦስትዮሽ ውይይት የተከናወኑ ስራዎች፣ የተስተዋሉ ችግሮች እና የእርምት እርምጃዎች ተነስተዋል።
የሰርቬይንግ ሥራዎች፣ የአፈር እና የብረት ጥናት ምርመራ፣ የቁፋሮ እና የኮንክሬት መሙላት ስራዎች መሠራታቸው በአማካሪ ድርጅቱ በኩል ተገልጿል።
ዶ/ር ብሩክ ባለፈው 1ወር ከ4ቀን የተሰሩ ስራዎች መልካም መሆኑን ገልጸው በተያዘው ቀንና በታቀደው ዕቅድ መሠረት ግንባታው እንዲከናወን በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ለዚህም ሥራውን ለማፋጠን በቀን እና በማታ ሁለት ሺፍት እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።