የአስራ ሰባተኛው ሳምንት የጥናትና ምርምር ጉባዔ በሁለት የጥናት ውጤቶች ላይ ተመስርቶ ተካሄደ፡፡ *****የካቲት 12/2017 ዓ.ም****

የአስራ ሰባተኛው ሳምንት የጥናትና ምርምር ጉባዔ በሁለት የጥናት ውጤቶች ላይ ተመስርቶ ተካሄደ፡፡
*****የካቲት 12/2017 ዓ.ም****
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 17ኛ ሳምንት የጥናትና ምርምር ሴሚናር የአገራችን ስልጠና ዘርፍ አካታችነት በተለይም የሴቶች ሚና ላይ ያተኮረ እንዲሁም ከዶሮ ላባ አልባሳትን መስራት የሚያስችል ቴክኖሎጂን የተመለከቱ ሁለት የጥናት ሰነዶች ላይ ተመስርቶ ውይይት ተደርጎበታል።
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ሳምታዊ ጉባኤ በተለያዩ ርዕሰጉዳዮች ገደብ ሳይደረግ ውይይት እያደረገ፣ እያወያየና ለተግባር የሚሆኑ ሀሳቦችን እያፈለቀ መምጣቱን የጥናትና ምርምር ኦና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።
በዚህኛው ሳምንታዊ ጉባኤም እንደሀገርም ብዙ ያልተሰራ ርእሰጉዳይን አካቶ እየተካሄደ መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ከUNESCO-China project ጋር በመተባበር የተዘጋጀውና Geneder Audit of FDRE TVT Institute and Its Satellite Campuses: Assessment Gender Equity and Inclusion የሚል ርዕስ የተሰጠው ጥናት በወ/ሮ አምሮት ይልማ ቀርቧል።
ጥናቱ በኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢና በሌሎች የስልጠና ካምፓሶች የሴቶች ሚና ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ያሳየና ወደፊት መሻሻል ያሉባቸውን ጉዳዮች ጠቁሟል።
ጥናቱ እንዳስመለከተው የሴቶች ተሳትፎ ለውጦች ቢኖሩትም ይበልጥ ሊሰራበት ይገባል።
በውይይቱ ላይ የጥናትና ምርምር ክፍሉ የስርዓተ-ጾታ ጉዳይን ትኩረት አድረጎ እንደሚያጠና የተገለጸ ሲሆን በሁሉም የስራ ዘርፎች የስርዓተ ጾታ ጉዳይ ተካቶ እንዲሰራ ዶ/ር ሀብታሙ አሳስበዋል።
ሁለተኛውና ጥናት በዶ/ር ጉሩሙርቲ እና ባልደረቦቻቸው የተዘጋጀ ሲሆን Sustainable Cold-weather Textiles &Textiles and Clothing: Harnessing Chicken Feather waste የሚል ርዕስ ተሠጥቶት ቀርቧል።
ይህ ጥናት የዶሮ ተረፈ ምርት የሆነውን ላባ ተጠቅሞ አልባሳት የማምረት ሀሳብ ይዞ መጣ ነው፡፡ ይህንንም ሐሳብ እውን ለማድረግ የኢንስቲትዩቱ በትኩረት እንዲሰራበት ምክረሐሳብ ቀርቧል።