ኢንስቲትዩቱ የብየዳ ስልጠናን በቨርቹዋል ሪያሊቲ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጥራትና ዘመናዊነቱን ለማስጠበቅ መዘጋጀቱ ተገለጸ። *******ጥር 05/2017******
ዓለምአቀፍ እውቅና ያለው የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል የብየዳ ስልጠና አሰጣጡን ለማዘመን ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ገልጸዋል።
ይህ ማሽን ዓለም የደረሰበትን የስልጠና ደረጃ ለማምጣት የሚያስችል ሲሆን ከስልጠና በኋላ ምዘና ሰርቶ የሚያሳውቅ በመሆኑ ይበልጥ ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና እና ምዘና ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።
የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሰላሙ ይስሃቅ እንደገለፁት ይህ ቴክኖሎጂ በስልጠና ወቅት የሚባክን ብረትን እንደሚቆጥብ የተገለጸ ሲሆን ሰልጣኞች ያለገደብ እንዲለማመዱ እንደሚያስችል ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ በብየዳ ስልጠና ሳይወሰን በርካታ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ስልጠናዎች መስጠት ያስችላል።
ኢንስቲትዩቱ በዛሬው ዕለት ያስጀመረው የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቴክኖሎጂን በስፋት ወደተቋሙ ለማስገባት ቴክኖሎጂው በግዢ ሂደት ላይ እንደሆነ ዶ/ር ብሩክ ተናግረዋል።