የሁለተኛ ዓመት ‹‹አንድ ተጨማሪ ክህሎት ለዜጎች›› የስልጠና መርሃ-ግብር ተጀመረ። ******ታህሳስ 14/2017******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመደበኛ እና በአጫጭር የስልጠና መርሃ-ግብሮች ከገበያ ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ ስልጠናዎችን በመስጠት ብቁ ዜጎችን ማፍራቱን ቀጥሏል፡፡
ሰው ተኮር ስራዎችን በማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራሙ ተደራሽ እያደረገ የሚገኘው ኢንስቲትዩቱ ‹‹አንድ ተጨማሪ ክህሎት ለዜጎች›› የሚል መርሃግብር ጀምሮ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የኢንስትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ የ2017 ዓ/ም ፕሮግራሙን በይፋ ባስጀመሩበት ሰዓት ኢንስቲትዩቱ በማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራሙ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና ተቋማትን እየደገፈ እንደሚገኝ ተናግረው ስልጠናዎችን በመስጠት ዜጎች ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በአራት የተለያዩ ሙያዎች ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ይህ የሁለተኛው መርሃግብር ገበያን ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ተፈጻሚ እንዲሆን የጥናትና ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ በአጽንኦት ገልጸል።
የውስጥ ሰራተኞችን ተጠቃሚ በማድረግ የጀመረው ‘አንድ ተጨማሪ ክህሎት ለዜጎች’ መርሐግብር አድማሱን እያሰፋ እንደሚቀጥልም ጨምረው ተናግረዋል።
ስልጠናዎቹ በግንባታ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ (Building Electrical Installation)፣ መሠረታዊ ሥነስዕል (Fundamental free hand drowing) ፣ ውሐ ስራዎች ላይ (Water Supply and sanitary) እና መሰረታዊ አውቶሞቲቭ ክህሎቶች (Autosafety) ላይ የሚሰጡ ሲሆን በሂደት በተለያዩ ክህሎቶች ላይም እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።
ቲክቶክ @fdretvtistitute
+7
All reactions:

39