ኢንስቲትዩቱ የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀመረ። **********ታህሳስ 4/2017********
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በኢንስቲትዩቱ የአካል ጉዳተኞች ማዕከልን ሥራ ያስጀመሩ ሲሆን ማዕከሉን ለማሳደግ በግብአት፣ በሰው ሐይል የተደራጀ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል ብለዋል።
አካል ጉዳት አለመቻል አይደለም ያሉት ዶ/ር ብሩክ ለዚህም በኢንስቲትዩቱ ያሉ አሠልጣኞች፣ ሰልጣኞች ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል። በአካል ጉዳት ምክንያት ከውጤታማነት ሳይጎድሉ ተልዕኮ ተሠጥቷቸው ተልዕኳቸውን በብቃት የሚወጡ አሠልጣኞች፣ ተመራማሪዎች፣ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
የተለያየ የአካል ጉዳት ያለባቸው የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችም ከህይወት ልምዳቸው ተነስተው ሠልጣኞች በአካል ጉዳታቸው ወደ ኋላ ሳይሉ ብቁ ሆነው መገኘት እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ማዕከሉ በዓለም አቀፍ ታህሳስ ወር የሚከበረውን የአካል ጉዳተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ እንደተከፈተም ተገልጿል።