የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አሰላሳዮች ቡድን የአገራችንን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጅ ለማዳበር የሚያስችል ምክረሐሳብ እያመነጩ ነው። ************ታህሳስ10/2017*********
የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ አሰላሳዮች ቡድን (TVT Thinktank Group) በረቂቅ ላይ የሚገኘውን የአገራችንን የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ማዳበር የሚያስችል ምክረሐሳብ ለማሰባሰብ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።
የአገራችን ቴ/ሙያ ሚሊዮኖችን አቅፎ የያዘ ዘርፍ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ዘርፉ ይበልጥ እንዲለወጥ እነዚህ አባላት የሚያዳብሩ እና የሚያሻሽሉ ሐሳቦችን ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በዚህም ላለፉት ወራት ባደረጓቸው ውይይቶች በርካታ ጠቃሚ ምክረሐሳቦች መገኘታቸውን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት በጀመረውና ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ውይይት በ2015 ዓ/ም የጸደቀው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መሠረት አድርጎ ረቂቅ ስትራቴጂ እንዲዳብር ወሳኝ ሐሳቦች ይጠበቃሉ ብለዋል።
የቲንክታንክ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ተሾመ ለማ ቡድኑ ከተለያዩ ተቋማት ስብጥር ያለው መሆኑን ገልጸው እነዚህ ምሁራን ከተለያየ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት የሚያመጧቸው ሐሳቦች ዘርፉን ለመለወጥ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ገልጸው ለዚህም በትጋት እየሠራን ነው ብለዋል።
ከረቂቅ ስትራቴጂው በተጨማሪ 2008 የወጣውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አዋጅ ለማሻሻል ምክረሃሳችን ማቅረብ፣ እና ዓለምአቀፍ የሥራ ድርጅት ያዘጋጀው የአዳዲስ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እሳቤዎች ሰነድ ላይ መወያየት አጀንዳዎች እንደሆኑ አንስተው ኢንስቲትዩቱ እና የተለያዩ ተቋማት የሚያደርጉላቸው እገዛም ይበልጥ እንደሚያበረታቸው ተናግረዋል።





