ኢንስቲትዩቱ ከፒክ የአይን ህክምና ክሊኒክ ጋር በመተባበር ለሰራተኞች የአይን ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ **************ታህሳስ 7/2017********

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከፒክ የአይን ህክምና ክሊኒክ ጋር በመተባበር ለሰራተኞች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የአይን ህክምና እና የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ክሊኒክ ሃላፊ አቶ ደረጀ ደገፉ ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸው ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማትም ሰራተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ሰራተኞች በስራ ባህርያቸው ምክንያት ከኮምፒውተር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አይናቸው ጉዳት ይደርስበታል ያሉት አቶ ደረጀ ከዚህ ችግር እንዲድኑ ቀድሞም እንዲጠነቀቁ ለማድረግ ፒክ የአይን ህክምና ክሊኒክ እየሰራ ያለውን ስራ አበረታች እና በሌሎች ተቋማትም ሊለመድ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የፒክ ቪዥን ማናጀርና ባለቤት ወ/ሪት ህሊና አበበ በበኩላቸው አስኮ አካባቢ የሚገኘው ክሊኒካቸው በአይን ጤና ላይ እየሰሩ መሆኑን ገልፀው በአካል ተገኝተው መታከም የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በስራ ገበታቸው ላይ ተገኝተው ህክምና እና የምክር አገልግሎት በመስጠት ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ ምርመራውን በነጻ እየሰጡ መሆኑን የገለጹት ማናጀሯ መነጽር ለሚያስፈልጋቸው አስር በመቶ ቅናሽ አድርገው እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ መሰል አገልግሎቶችን በተለያዩ ተቋማት ላይ እየሰጡ እንደሚገኙና ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ይህንን በማድረጋቸውም ታላቅ ክብር እንደሚሰማቸው ተናግረዋል፡፡