ኢንስቲትዩቱ በሲዳማ ክልል ከሚገኙ ኮሌጆች ለተወጣጡ መሪ አሠልጣኞች ያዘጋጀው ስልጠና ተጠናቀቀ። ***********ታህሳስ 5/2017********

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በክልሉ ከሚገኙ ኮሌጆች ለተውጣጡ መሪ አሠልጣኞች በlnnovative Pedagogy እና በProfessional ldentity ላይ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊና ሙያ ስልጠናና ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍስሀ ፍቾላ ስልጠናው በክህሎትና በሙያ የበቁ ባለሙያዎች እና አሰልጣኞችን ለማፍራት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል ።
ስልጠናውን አሠልጣኞች ዶ/ር ይስሀቅ እና አቶ ኢብራሂም የሠጡ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም የወሰዱት ስልጠና ወሳኝ መሆኑንና ከስልጠና የተሻለ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀው እንደዚህ ዓይነት ስልጠና በየጊዜው መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።
ስልጠናው ቀጣይነት እንደሚኖረው ተገልጿል
መረጃው የሲዳማ ክልል የህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት ነው።
ቲክቶክ @fdretvtistitute