ኢንስቲትዩቱ በደረጃ ስምንት ስልጠና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ። ************ህዳር 18/2017*********

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ/ም አጋማሽ በሁለት ፕሮግራሞች በደረጃ ስምንት ስልጠና መስጠት እንደሚጀምር የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ገልጸዋል።
ከደረጃ ስድስት እስከ ስምነት የማሰልጠን ተልዕኮ የተሰጠው ኢንስቲትዩቱ በደረጃ ስድስትና ሰባት ብቁ ሙያተኞችን እያፈራ እንደሚገኝ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ በተያዘውም ዓመት አጋማሽ እንደአገር ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ ስምንት በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ እና በቴክኒክና ሙያ አመራር መስኮች ማሰልጠን እንደሚጀምር ተናግረዋል።
ይህንን አገራዊ ቁልፍ ተግባር ለመፈጸም ኢንስቲትዩቱ የሪፎርም ቡድን አዋቅሮ ሲዘጋጅ መቆየቱን ገልጸው በቀሪ ወራትም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን በማካሄድ የሚገኙ ግብአቶችን የማካተትና ስልጠናውን የመጀመር ስራ ይሰራል ብለዋል።
ለውይይት የሚሆን ፕሮፓዛል የቀረበ ሲሆን የፕሮግራሞቹ አግባብነት፣ የሰውሐይል እና የቁሳቁስ ሀብቶች፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና ሌሎች ጉዳዮች ተዳስሰዋል።
ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ሰዓት በደረጃ ስድስት 22 እንዲሁም በደረጃ ሰባት በ19 ፕሮግራሞች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።