በክህሎት ኢትዮጵያ እየተሳተፉ ያሉ ዜጎች በስነምግባርና በአገርፍቅር ላይ ያተኮረ ግንዛቤ እና ማብራሪያ እየተሰጣቸው ነው። ህዳር 16/2017 ዓ.ም

በክህሎት ኢትዮጵያ እየተሳተፉ ያሉ ዜጎች በስነምግባርና በአገርፍቅር ላይ ያተኮረ ግንዛቤ እና ማብራሪያ እየተሰጣቸው ነው።
ህዳር 16/2017 ዓ.ም
ዜጎች በተለይም ወጣቶች በቴክኖሎጂና በፈጠራ ስራ የተሻለ አበርክቶ እንዲያደርጉ የሚያስችለው የክህሎት ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር ቴክኖሎጂ የማበልጸጊያ መርሃ-ግብር በኢንስቲትዪቱ ከተጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል።
መርሃ-ግብሩ ተሳታፊዎች በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ ስነምግባርና የአገር ፍቅር የተላበሱ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚያግዝ ነው።
መርሃ-ግብሩን እየፈጸሙ ያሉት ከኢትዮጵያ የፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የመጡ የፖሊስ አመራር አካላት ሲሆኑ የቴክኖሎጂ አበልጻጊ ባለሙያዎች ለአገርና ለራሳቸውም ጠቃሚ ዜጋ ይሆኑ ዘንድ በስነምግባርና በአገርፍቅር ስሜት ስራዎችን ለመፈጸም የሚያስችል ተነሳሽነት እንዲያገኙ ግንዛቤና ማብራሪያ እየሰጡ ናቸው ።
በክህሎት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር ተሳታፊዎች ሰማኒያ ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን ሰርተው ማበርከታቸው ይታወሳል።
ቲክቶክ @fdretvtistitute
+4
All reactions:

39