የአገራችንን የግንባታ ኢንደስትሪ በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና የሠው ሐይሉን ለማብቃት ያለመ የላቀ ትብብር። *****************ጥቅምት 20/2017********
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በአገራችን የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ አዲስ ባህል እየፈጠረ ከሚገኘው የኦቪድ ግሩፕ በጋራ የግንባታ ኢንደስትሪውን በሰው ሐይልና በቴክኖሎጂ ለማዘመን በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የኦቪድ ግሩፕ የበላይ ሀላፊ ከሆኑት አቶ ዮናስ ታደሰ ጋር ተቋማቱ በትብብር ለመስራ የሚችሉበት ጉዳይ ላይ መክረዋል። ትብብራቸውም በስልጠና እና በቴክኖሎጂ ላይ እንደሚያተኩር የገለጹት ዶ/ር ብሩክ ኢንስቲትዩቱ የዘርፉን የሠው ሐይል አቅም ለማሳደግ ብቁ ሙያተኞች ያፈራል ብለዋል። ከዚህም ሌላ በኢንስቲትዩቱ እየተመረቱ ያሉ የግንባታ ኢንደስትሪውን የሚያዘምኑ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ዘርፉን ለማዘመን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ራዕያችን ልማት ነው ወይም Our Vision is Development (OVID) በሚል የሚታወቀው ድርጅት ሀላፊ አቶ ዮናስ ታደሰ በበኩላቸው ተቋማቸው በሙሉ አቅሙ ወደስራ ሲገባ እስከ 200ሺህ የሠው ሐይል የስራዕድል እንደሚፈጥር ገልጸው የኢንስቲትዩቱ የሠለጠነ የሠው ሐይል እንዲያቀርብለት ፍላጎት እንዳለው ገልጸው ኢንስቲትዩቱም ይህንን እንደሚወጣ የሚያስችል አቅም እንዳለው ተናግረዋል።
ተቋማቸው በኢንስቲትዩቱ እየተፈጠሩ ያሉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ተመርተው የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን እንዲያዘምኑ እና እንዲያቀላጥፉ ለማስቻል ምቹ መደላድል ይፈጥራል ብለዋል።