የኢንስቲትዩቱ ስቴም ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞችን ተቀበለ። ነሀሴ 07/2016 ዓ.ም

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ ላይ ወጣቶችን ለላቀ የፈጣራ ሃሳብና ልምድ የሚያሳድገው የስቴም ስልጠና ማዕከል ዛሬ የመጀመሪያ ዙር ወጣቶችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀምሯል።
የስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ይህ ስልጠና የመጀመሪያ መሆኑን አስታውሰው ከአሁን በኋላ የአከባቢውን ወጣቶች ተከታታይ ስልጠና መስጠት እንደሚቀጥሉበት ተናግዋል።
ዓለማችን እየመሩ ያሉ ሰዎች በዋናነት የክህሎትና የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ስልጠና ወጣቶች ያላቸውን ፍላጎትና ችሎታ እንዲያሳድጉ ተነሳሽነት ለመፍጠር ይጠቅማል ብለዋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይም ወጣት ሰልጣኞች አንድ የፈጠራ ሀሳብ ይዘው እንደሚወጡ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ በበኩላቸው የኢንስቲትዩቱ ስቴም ማከል ሙያዊ ክህሎትን ከፍ እንዲያደርግ ተደርጎ የተደራጀ በመሆኑ ወጣቶች ያላቸውን ክህሎት እንዲያሳደጉ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል።
የኤፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስቴም ማዕከል በአገሪቱ 69ኛ የስቴም ስልጠና ማዕከል ሆኖ ዘንድሮ ተከፍቷል።