የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ጥራት ባለው ሁኔታ እንዲካሔድ በደህንነት ካሜራዎች ጭምር ታግዞ ክትትል ሲደረግ እንደነበር ተገለፀ፡፡
በኢንስቲትዩቱ እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ጥራት ባለው ሁኔታ እንዲካሔድ በደህንነት ካሜራዎች ጭምር ታግዞ ክትትል ሲደረግ እንደነበር ተገለፀ፡፡
በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ/ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ከተለያዩ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተውጣጡ ተማሪዎችን ፈተና ሲሰጥ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ያሟላቸው የደህንነት ካሜራዎች እና የአይሲቲ መሰረተ ልማቶች የፈተና ሂደቱ ደህንነቱ በተጠበቀ እና ኩረጃን ሊከለከል በሚችል አግባብ እንዲካሔድ ማስቻላቸው ተገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎች በቆታቸው ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን በእነዚህ መሰረተልማቶች ታግዞ ሲሰራ ነበር ተብሏል፡፡
ተማሪዎች በቆይታቸው አስፈላጊ ግብአቶች ተሟልቶላቸው መልካም ቆይታ እንዲኖራቸው ሲሰራ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን የፈተና ሂደቱን ፍጹም የተሳካ ለማድረግ ኢንስቲትዩቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ሲሰራ መሰንበቱ ተገልጿል፡፡