ኢንስቲትዩቱ አዲስ ባዘጋጀው መዋቅራዊ ጥናት ላይ ለሀዋሳ ካምፓስ አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ። *******ግንቦት 17/2016 ዓ.ም*******

ኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተሰጠውን ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችል ሲቪል ሰርቪስ መዋቅር ለመፍጠር አዲስ አደረጃጀት አስጠንቶ ማጠናቀቁን ተከትሎ ተመሳሳይ ግንዛቤ ደረጃ ላይ የሚያደርሱ ተከታታይ የስልጠና መድረኮችን እያካሄደ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ለሃዋሳ ካምፓስ አመራሮች እና ሙያተኞች በአዲሱ አደረጃጀት እና በፌደራል መንግስት ሠራተኞች ድልድል አፈፃፀም መመሪያ ላይ ስልጠናው ተሰጥቷል።
የካምፓሱ ኃላፊ አቶ #ፍፁም_ግርማ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ኢንስቲትዩቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀድሞ ከነበረው እጅግ የተሻለና በቀጣይ ዓመታት በጥሩ ሁኔታ ሊያሰራ የሚችል መዋቅር ለካምፓሱ በማዘጋጀትና በማፀደቅ ወደ ሥራ እንዲገባ በማድረጉ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ ግልፅና ፍትሀዊ የድልድል ሂደት እንደሚኖር አስገንዝበዋል፡፡
ሥልጠናው በሠራተኞች ድልድል ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ #ወንድራድ_በኃይሉ እንዲሁም በሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ #ዳንኤል_አሊ የተሰጠ ሲሆን ሠራተኞችም የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ተጠናቋል፡፡
ተመሳሳይ የስልጠና መድረክ በኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢ ለአመራሮች እና ሙያተኞች ተዘጋጅቶ ስልጠና መሠጠቱ የሚታወስ ነው።
መረጃው የካምፓሱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።