የኢንስቲትዩቱ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) ከሁሉም ዓመት ከየትምህርት ክፍል ተወካይ ተማሪዎች ጋር ውይይት አካሒዱ።
በርከት ያሉ ጉዳዮች በተነሱበት በዚህ መድረክ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኢንስቲትዩቱ የሚሰጥ በመሆኑ የሚያጋጥምን የአካዳሚክ ካሌንደር ለውጥ እንዴት በአግባቡ መፈጸም እንደሚገባ በስፋት ምክክር ተደርጎበታል። በተጨማሪም የመውጫ ፈተናን ፣ ጥራት ያለው ስልጠና አሰጣጥን፣ የተማሪዎች መመረቂያ ፕሮጀክቶች፣ የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎቶች ጉዳይ እና ሌሎችም ሐሳቦች በተወካዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ተመሳሳይ ግንኙነቶችን በማዘጋጀት የተጠየቁ ጥያቄዎች የተመለሱበት አግባብ ለውይይት እንደሚቀርብ ረ/ፕሮፌሰር ሐፍቶም ገልጸዋል።