የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ባህል ብዙ ተቋማት ከአንስቲትዩቱ ጋር በዘርፉ ላይ አብረው እንዲሰሩ ፍላጎት እንዲያድርባቸው እያደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲተዩት 29ኛ ሳምንት የጥናትና ምርምር ሴሚናር በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ማለትም የመጀመሪያው “The Future of Entrepreneur Innovation: Harnessing the Power of Emerging Technologies and “the Power of Mathematics”, በሚል በ #መንግስቱ_ጫልቺሳ (ረ/ፕሮፌሰር) ሁለተኛው “Work Ethics and Professionalism in TVET Setting” በሚል ርዕስ በ #ዳንኤል_አባተ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳሬክተር የሆኑት ዶ/ር #ሐብታሙ_ሙሉጌታ ሴሚናሩን በንግግር ሲከፍቱ በሴሚናሩ የሚቀርቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች ከጥናትና ምርምር፣ ከቴክኖሎጂ ባሻገር የቴክኒክና ሙያ የስልጠና ስርዓቱን የሚያጎለብቱ ጽሁፎች ናቸው ብለዋል፡፡
የሂሳብ ትምህርት ከቴኖሎጂ እና ሳይንስ ጋር አገናኝተን የመገንዘብ እና የመተንተን ጉድለቶችን ለመቅረፍ፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና በቀጣይም የበለጠ እንዲሰራበት ለማንቃት የመጀመሪያው ጽሑፍ ፍንጭ የሚሰጥ ጥናት ነው ብለዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ STEM ማዕከል ከፍቶ እየሰራ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
በተጨማሪም እንደአገር የፐብሊክ ሰርቪስ ለማዘመን በሚሰራው ስራ ፕሮፌሽናል ሲቪል ሰርቫንት አስፈላጊ በመሆኑ እንደአገር በአዲስ መልክ እየተሰራበት ይገኛል ያሉ ሲሆን፡፡ ሁላችንም ከፕሮፌሽናል ሲቪልሰርቫንት አኳያ ራሳችንን ማዘጋጀት ይገባናል ብለዋል፡፡ ሁለተኛው ጽሑፍ ከዚህ አኳያ የሚያተጋን ይሆናል ብለው እንደሚምኑ ገልጸዋል፡፡
እንደ ዶ/ር ሐብታታ ገለጻ ኢንስቲትዩቱ ባህል ባደረገው የጥናትና ምርምር ስራ ተቀባይነቱ በማደጉ ከተቋሙ አልፎ ለአገሪቱ እድገት አጋዥ የሚሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ትስስሮች ተጀምረዋል፡፡