ተቋማዊ አቅሞችን በማቀናጀት ተኪ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ለማምረት ያለመ ትብብር ። **********ግንቦት 13*********

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር #በአሚዮ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና #በሀምድ ጀነራል ማሸነሪ ስራዎች ኢንተርፕራይዝ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ውይይት እና ጉብኝት አካሄዱ።
ዋና ዳይሬክተሩ እና የተለያዩ የስራ ክፍል ሀላፊዎች ባደረጓቸው በእነዚህ የመስክ ጉብኝት እና የትብብር ውይይቶች ተቋማቱ ያላቸውን የሰው ሀይል እና ቁሣዊ ሀብት በማስተሣሠር ከውጪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን በአገር ውስጥ በስፋት ማምረት ለማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።
ዶ/ር ብሩክ ኢንስቲትዩቱ በሠመር ካምኘ እና በመደበኛ ፕሮግራም ቴክኖሎጂዎችን በስፋት እያተመረተ መሆኑን ገልፀው የሚመረቱ ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋት እንደነዚህ አይነት ትስስሮችን ፈጥሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
ትስስሮቹ በዋናነት ሁለት ማዕቀፎች ላይ የሚያተኩር ሲሆን አንዱ የቢዝነስ ትስስር ሲሆን ይህም በተለይም ድርጅቶቹ ከኢንስቲትዩቱ የቴክኖቢዚያ ኢንተርፕራይዝ ጋር የሚተሳሰሩበትን ሁኔታ የሚይዝ ሲሆን ሌላኛው የትብብር ማዕቀፍ የክህሎት ልማት ስራዎች ላይ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በፍላጎት እና በጥናት ላይ የተመሠረቱ ስልጠናዎችን የሚሰጥበት እንደሚሆን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።