አራተኛው አህጉርአቀፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ኮንፈረንስ በኢንስቲትዩቱ መካሄድ ጀመረ።
አራተኛው አህጉርአቀፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ኮንፈረንስ በኢንስቲትዩቱ መካሄድ ጀመረ።
***************ግንቦት 10/2016**************
የኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ማህበር ያሰናዳውና ለሁለት ቀናት የሚቆየው ኮንፈረንስ ‹‹የአፍሪካ የመምህራን ማህራትን ማብቃት፣ የእንግሊዝ ቋንቋ ስልጠናን በ21ኛው ክ/ዘመን ክህሎቶች መቃኝት›› (Empowering African Teachers’ associations and Enhanced English Language Training through 21st Century Skills) በሚል መሪ መልዕክት መካሄዱን ጀምሯል።
በኮንፍረንሱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር ትምህርት እና ስልጠና የእድገት መሰረት እንደሆነ ገልጸው አስተማሪዎቻችንን ማብቃት አፍሪካን ማብቃት ነው ብለዋል ይህም የሆነው በአፍሪካ ውስጥ አስተማሪዎቻችን አስተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አማካሪዎች፣ አርአያዎች እና በማህበረሰባችን ውስጥ የለውጥ አራማጆች በመሆናቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አስተማሪዎች ሁልጊዜም ዘመኑ የሚጠይውን ክህሎት በመጨበጥ ብቁ ሆነው በመገኘት ለሚሊዮኖች ተማሪዎቻቸው የመማር ፍላጎት ማሳደግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ለመምህራንም እውቅና መስጠት እና ለኑሮና ለሥራቸው የተመቸ ከባቢ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በኮንፍረንሱ ላይ ከኬኒያ፣ ከታንዛኒያ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከብሩንዲ፣ ከሩዋንዳ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከዲሞከራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከኡጋንዳ፣ ከዛንዚባር እና እና ከአፍሪካ ውጪም ከተለያዩ አገራት ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ኮንፍረንሱ ለሁለት ቀናት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እየመከረ እንደሚገኝ ከፕሮግራሙ ማወቅ ተችሏል፡፡