ኢንስቲትዩቱን በአገርአቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖርት ውድድር የሚወክሉ የስፖርት ልዑካን ሽኝት ተካሄደ።

ኢንስቲትዩቱን በአገርአቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖርት ውድድር የሚወክሉ የስፖርት ልዑካን ሽኝት ተካሄደ።
**********ጥር 14/2018****
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በአገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ውድድር ለሚሳተፉ የኢንስቲትዩቱ የስፖርት ልዑካን አባላትን አሸኛኘት አድርገዋል።
ዶ/ር ብሩክ ባሳለፍነው ዓመት በተካሄደው ውድድር ላይ ውጤት መመዝገቡን አስታውሰው በዚህ አመትም ተጠናከሮ እንዲቀጥል አበረታትተዋል።
በአገራችን የቴክኒክያ ሙያ ስርዓት ውስጥ ብቸኛ የከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ያለው ኢንስቲትዩታችን ስሙ ከፍ ብሎ እንዲተዋወቅ መልካም ውጤት በማስመዝገብ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ዋና ዳይሬክተሩ አደራ ብለዋል።
በሥነሥርዓቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን በአራት የስፖርት አይነቶች ማለትም በቴክዋንዶ፣ በቼዝ፣ በጠረጴዛ ቴንስ፣በሩጫ እንደሚሳተፍ ተገልጿል።