20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ሁነቶች ተከበረ::

20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ሁነቶች ተከበረ።
******ህዳር 29/2018******
“ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት በአገራችን ለ20 ጊዜ የተከበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በኢንስቲትዩቱ በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በመልዕክታቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን በባህል፣ በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት የደመቅን ውብ ህዝቦች ነን ብለዋል።
ኢንስቲትዩታች ከሁሉም ማዕዘናት የመጡ ኢትዮጵያዊያን ስለሚገኙ ትንሿ ኢትዮጵያ ማለት እንችላለን ያሉት ዶ/ር ብሩክ ሠልጣኞች በቆይታቸው አንዱ የአንዱን ባህል አንዱ ያንዱን ማንነት ሌላው አውቆ እና አክብሮ መኖር እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሁሉም ዜጎች በየተሰማራንበት የሥራ መስክ ኢትዮጵያችንን ከፍ የሚያደርግ እንደሚገባ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ የክህሎት ልማቱ አገራችንን ወደ ከፍታ የሚመራ እንዲሆን በትጋት መሥራት ይገባል ብለዋል።
በበአሉ ላይ የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች የተለያዩ ትርኢቶችን አቅርበዋል።