ኢንስቲትዩቱ የብየዳ ሙያተኞችን በስፋት ማሰልጠኑን እንደሚቀጥል ተገለጸ።
ኢንስቲትዩቱ የብየዳ ሙያተኞችን በስፋት ማሰልጠኑን እንደሚቀጥል ተገለጸ።
***ህዳር 22/2018*
የኢፌዲሪ ቴስኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በፊሌት ዌልዲንግ
(fillet Welding) በሞጁል 1 እና 2 የዓለምአቀፍ የብየዳ ስልጠና ወስደው ላጠናቀቁ ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷል።
በእውቅና አሰጣጥ መርሀግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ ኢንስቲትዩቱ በብየዳ ሙያ ብቁ አሰልጣኞችን እና የኢንዱስትሪ ቴክኒሺያኖችን ለማፍራት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት ጊዜው በሚፈልገው ጥራት ልክ እያሳደጉ መሄድ ይገባቸዋል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሯ ኢንስቲትዩቱ ከተቋማት ጋር በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።
ወ/ሮ ፀዳለ አያይዘውም የብየዳ ሙያተኞችን በብዛት በማሰልጠን የአገራችንን ኢንደስትሪዎች ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ ለተለያዩ አገራት የሰለጠነ የሰው ሀይል አገራችን እንድትቀርብ ያስችላታል ብለዋል።
በቀጣይ የሰልጣኞችን ቁጥር በማሳደግ ስልጠና እንደሚሰጥም ጨምረው ገልጸዋል።
በእለቱ ከሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተገኙት ኮ/ል ቢቂላ በቃና ሰልጣኞቻችን ብቁ ባለሙያዎች እንዲሆኑ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
የስልጠና አሰጣጡን በቅርበት እየተከታተሉት እንደነበር ገልጸው በስልጠና ጥራቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ትብብሩን በማስቀጠልም ባለሙያዎቻቸውን ለመሠል ስልጠና እንደሚልኩ ገልጸዋል።
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ; https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
facebook https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/@fdretvtistitute





