ኢንስቲትዩቱ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር የቢዝነስ ፓርትነርሺፕ መመስረት በሚችልበት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
ኢንስቲትዩቱ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር የቢዝነስ ፓርትነርሺፕ መመስረት በሚችልበት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
******ህዳር 16/2018*****
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ሀላፊ ዶ/ር አንዷለም አድማሴ ጋር በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች አብሮ ለመስራት ተወያይተዋል።
ዶ/ር ብሩክ፣ ኢንስቲትዩቱ ተኪ ቴክኖሎጂዎችን የማምረት ልምምድ ያለው መሆኑን አንስተው ሁለቱ ተቋማት በሚፈጥሩት ትብብር በቴሌኮም ዘርፉ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለማምረት የሚያስችል ሥራ ይሠራሉ ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት ረገድ በዘርፉ ተፈላጊና ተወዳዳሪ ሙያተኞችን እናፈራለን በማለት ተናግረዋል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ሀላፊ ዶ/ር አንዷለም ኢንስቲትዩቱ ያለው የተደራጀ ወርክሾፕ፣ በኢንተርፕሬይዙ በኩል ያለው የቢዝነስ ልምምድ ለተቋማቸው ምቹ ፓርትነር እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።
የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ ኢንስቲትዩቱ የድርጅቱን የቴክኖሎጂ ፍላጎቶች የሚመልስ በጊዜና በጥራት የመስራት ዝግጁነት እንዳለው አረጋግጠዋል።
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ; https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
facebook https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/@fdretvtistitute





