ኢንስቲትዩቱ በመጀሪያው ሩብ ዓመት በርካታ ውጤቶች ማስመዝገቡ ተገለጸ።
ኢንስቲትዩቱ በመጀሪያው ሩብ ዓመት በርካታ ውጤቶች ማስመዝገቡ ተገለጸ።
*******ህዳር8/2018******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ውይይት ተካሄደ።
ውይይቱን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በየሩብ ዓመቱ የሚደረግ የተግባራት ግምገማ የተሰጡ ተግባራትን በስኬት ለመፈጸም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የጥራት ዓመትን ለማሳካት ጅምራችንን ለመፈተይ ያስችላል ያሉት ዶ/ር ብሩክ በሩብ ዓመቱ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት እንደሆነ አንስተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህ ዓመት የ5ዓመታት ዕቅድ ዘመን ማጠቃለያ የቀጣይ 10 ዓመታት እቅድ የሚዘጋጅበት ዓመት እንደመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሻል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በስልጠና፣ በጥናትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት የተመዘገቡ ውጤቶችን አንስተዋል።
የኢንስቲትዩቱ የአስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አዋቶ የ1ኛ ሩብ ዓመትን ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፖርታቸውም የአገልግሎት አሰጣጥ ስራትን ለማሻሻል መሰራቱን በዚህም የISO 9001:2015 ትግበራ ማስቀጠል መቻሉን ጠቅሰዋል።
ሠራተኞችን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ የሠራተኞች የሥራ ላይ ስልጠና ተዘጋጀቱንም ጨምረው ገልጸዋል።
የመንግስት ሰራተኞች የሪፎርም የትግበራ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
የስልጠና ጥራት አግባብነትና ተደራሽነትን በማሳደግ ረገድ ኢንስቲትዩቱ ሰፊ ሥራ መስራቱን አቶ ኤልያስ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።
አዳዲስ ፕሮግራሞች የተቀረጹበት እና ስልጠና የተጀመረበት ሩብ ዓመት መሆኑን አንስተው ኢንስቲትዩቱ አዳዲስ እና ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ስልጠና መስጠት ጀምሯል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ዓለማቀፋዊነቱን ለማስፋት በሠራው ውጤታማ ስራ ወደ አልጀሪያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሠልጣኞችን መላኩን ሌላው በስኬት ያነሱት ነው።
ጥናትና ምርምር ሳምንታዊ ምርምር ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ኢንስቲትዩቱ በሩብ ዓመቱ ያስመዘገበው ሌላው ስኬት ሆኖ ተጠቅሷል።
በዚህም ለስልጠና ጥራት የሚያግዙ ለተለያዩ ዘርፎች መሻሻል የሚያስችሉ የጥናት ውጤቶች እየቀረቡ መሆኑ ተገልጿል።
ከቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት አንጻር ሠፊ ስራዎች መመዝገባቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የተዋወቁበት ሩብ ዓመት መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ 7 አዳዲስ የአሰራር ስርዓት ሰነዶች መዘጋጀታቸው ተመላክቷል።
በሩብ ዓመቱ ከ13 በላይ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር መፈጠሩ የተጠቀሰ ሲሆን ኢንደስትሪዎች በካሪኩለም ዝግጅት ጭምር መሳተፋቸው ተገልጿል።
ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ በቴክኖሎጂ ማስ ፕሮዳክሽን የተሰማራበት ሩብ ዓመት መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል።
የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳታፊዎች በተለያዩ ዓለምአቀፍ መድረኮች በመወዳደር እና በማሸነፍ የአገራችንን ስም ያስጠሩበት ጊዜ እንደሆነም ተነስቷል።
የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ በሩብ ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች አመርቂ መሆናቸውን አንስተዋል።
የመጣው ለውጥ ጥሩ መሆኑን ገልጸው የጥራት ዓመትን ለማሳካት መቀናጀት ዘርፎች ማስተሳሰር ይገባል።
የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ በበኩላቸው አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞቻችን በጣም ተመራጭ እንዳደረጉን ይህም የገበያውን ፍላጎት መረዳታችን ማሳያ ነው ብለዋል።
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ; https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
facebook https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/@fdretvtistitute





