ኢንስቲትዩቱ ለዲቦራ ፋውንዴሽን የአልባሳት ድጋፍ አደረገ። ****ህዳር/03/2018 ዓ.ም******
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) በዲቦራ ፋውንዴሽን የሥራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ክፍሎች የተመረቱትን ጨምሮ ግምታቸው 1ሚሊዮን ብር የሚያወጡ አልባሳትን አበርክተዋል።
ዶ/ር ሀብታሙ፣ ከፋውንዴሽኑ መስራችና ባለቤት ክቡር አቶ አባዱላ ገመዳ ጋር ሁለቱ ተቋማት በጋራ መስራት ስለሚችሉባቸው ጉዳዮች ተነጋግረዋል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኢንስቲትዩቱ በስልጠና፣ በጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ ልማት አተኩሮ እንደሚሠራ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በማህበረሰብ አገልግሎት መስክ ከሚሰራቸው መካከል ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች እንደ አእምሯዊና አካላዊ አቅማቸው የሚመጥን አካታች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ይህም ዲቦራ ፋውንዴሽን የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ዜጎች ለሚሰጠው ስልጠና ቅርበት እንዳለው ገልጸው ኢንስቲትዩቱ ከዚህ አንጻር አብሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች ክቡር አባዱላ ገመዳ፣ ኢንስቲትዩቱ ፋውንዴሽኑን በመጎብኘቱና ድጋፍ በማድረጉ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ፋውንዴሽኑ የአእምሮ ውስንነት ላሉባቸው ሰዎች የሙያ ማሰልጠኛ ስራን እያሰፋ ስለሚሄድ ከኢንስቲትዩቱ የስልጠና ድጋፍ በይበልጥ ይፈልጋል ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ ልዑክ የህጻናት መማሪያ፣ የክህሎት ስልጠና ፣ የህክምና ፣ የፊዚዮቴራፒ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የእንስሳት እርባታ ማዕካላትን ጉብኝት አድርጓል።





