ኢንስቲትዩቱ ከአልጀሪያ መንግስት የተገኘ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ ለሆኑ የደረጃ 6(መጀመሪያ ዲግሪ) ሰልጣኞች የሽኝት መርሀግብር አካሄደ። *********ጥቅምት 22/2018**********
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስልጠናና አቅም ግንባታ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) ይህ የግለሰቦች ትምህርት ጉዳይ ብቻ አይደለም አገርን በዓለምአቀፍ መድረክ የመወከል፣ ለዘርፉ ተጨማሪ አቅም የመፍጠር ጉዳይ ነው ብለዋል።
የአልጀሪያ ህዝብና መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ያበረከቱት ይህ ስኮላርሺፕ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቅርብ ክትትል እውን መሆን ችሏል ያሉት ሐፍቶም (ረ/ፕሮፌሰር) ለዚህም ክብትር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ላደረጉት አመራር ሰጪነት ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኢንስቲትዩቱ ለአገራችን የግብ ስኬት ቁልፍ ዘርፍ ለሆነው የክህሎት ልማት የመሪነት ሚና የሚወጣመሆኑን ገልጸው በዚህ ዕድል የሚጠቀሙ ወጣቶ ሲመለሱ የሚጨምሩት አቅም ብዙ ነው ብለዋል።
ተማሪ ታምራት ወንድምኩን እና ተማሪ ትህትና ለተሰጣቸው እድል አመስግነው በመጀመሪያ ኢንስቲትዩቱን መርጠው መግባታቸው በብዙ መንገድ እንደጠቀማቸው ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ፣ ውጤታማ ተማሪዎች ሆነን አገራችን የሰጠችንን አደራ በብቃት ተወጥተን ህዝባችንን ለመጥቀም ቃል እንገባለን ብለዋል።
በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና አቅምግንባታ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) ከአደራ ጋር የአገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በክብር አስረክበዋል።





