የኢንስቲትዩቱ የ2018 ዓ/ም ሳምንታዊ የጥናትና ምርምር ምርምር ጉባኤ ተጀምሯል::

“ኢንስቲትዩቱ በሳምንታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤዎች በዓለም እና በአገራችን የወደፊቷ አበይት ክስተቶች (Mega Trends) ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል”
(ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ- የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር)
*****መስከረም 05/2018ዓ.ም******
የኢንስቲትዩቱ የ2018 ዓ/ም ሳምንታዊ የጥናትና ምርምር ምርምር ጉባኤ ተጀምሯል።
ጉባኤን ያስጀመሩት የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ባሳለፍናቸው 2 ዓመታት በተደረጉ ተከታታይ ጉባኤዎች ስኬታማ የነበሩና በርካታ ውጤቶች የተገኙባቸው እንደነበሩ አስታውሰዋል።
በእነዚህ ጥናትና ምርምሮች የስልጠና ዘርፋችንን ጥራት እና አግባብነት የሚያሻሽሉ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉት ዶ/ር ሀብታሙ በቴክኖሎጂ ዘርፉ የተጀማመሩ ቢኖሩም በያዝነው ዓመት ለቴክኖሎጂ ፈጠራ የሚበጁ ምርምሮችን ማድረግ ትኩረት አድርገን የምንሰራው ይሆናል ብለዋል።
በስልጠናው መስክ በተሠሩ ተከታታይ ምርምሮች መነሻ በማድረግ ገበያን መሠረት ያደረጉ የአዳዲስ ፕሮግራሞች እንዲከፈቱ፣ ነባሮቹ እንዲከለሱ እንዳስቻሉ አያይዘው ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በያዝነው ዓመት የዓለምን እና የአገራችንን አበይት እክስተቶች (Mega Trends) ላይ አተኩሮ ማዘጋጀት የዚህ ዓመት አንዱ ትኩረት እንደሆነ ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
እነዚህ እሳቤዎች አገራችን ዓለም ወደደረሰብ ደረጃ ለመስፈንጠር የምታልመውን ጉዞ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ መተንተን ይገባል፤ ስልጠናዎቻችን፣ ቴክኖሎጂዎቻችን ከዚህ አንጻር እንዲቃኙ ለማድረግ የሚያግዙ ጥናቶችን ማጥናት ይገባል ብለዋል።
ዓለማቀፋዊነት ሌላው የትኩረት ነጥብ እንደሚሆን አመላክተው በዓለምአቀፍ መድረኮች ምርምሮችን ማቅረብ፣ የኢንስቲትዩቱን ጆርናል ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ማጠናከር፣ በዘርፉ ዓለምአቀፍ ትብብር ማድረግ ከዚህ አንጻር እንደሚተኮርበት ገልጸዋል።
በሦስተኛነት የፖሊሲ አተገባበርን የሚፈትሹ ምርምሮች ሲሆኑ ይህንንም ከተጀመረው በላይ ይበልጥ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።
ትስስር አራተኛው የትኩረት ነጥብ እንደሆነ የገለጹቱ ዶ/ር ሀብታሙ እንደተቋም የዘርፎች ትስስር፣ በተቋማት መካከል ያለ ትብብር፣ ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር ትብብር ለጥናትና ምርምር ዘርፉ ትኩረት እናደርጋለን ብለዋል።
በዛሬው የመክፈቻ ጉባኤ ላይ አበይት ክስተቶችን ( mega trends ) በመመልከት መጻኢ ክህሎቶችን ማበልጸግ ላይ የሚያተኩር Navigating Megatrends: Bridging Policy, Skills, and Governance Gaps for Ethiopia’s Socio-Economic Future የሚል ርዕስ የተሰጠው ፕሮፖዛል በድንቁ ገበየሁ (ዶ/ር) ቀርቧል። በቀረበው መነሻ ጽሁፍ ላይም ውይይትና ሀሳብ ልውውጥ ተደርጓል።
በመጨረሻም ባሳለፍነው ዓመት ለነበሩ ጉባኤዎች ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ፋካሊቲዎችና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።