የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ከስራ ክፍሎት በቀረበ ሪፖርት መሠረት ገምግመዋል።

‘’ተሞክረው የማያውቁ ከውጭ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን የሚተኩ የፈጠራ ስራዎችን በሩብ ዓመቱ መፍጠር ተችሏል”
(የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ)
******መስከረም 30/2018ዓ.ም*****
የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ከስራ ክፍሎት በቀረበ ሪፖርት መሠረት ገምግመዋል።
በዘርፉ ያሉ የስራ ክፍሎችና የፋካሊቲ አስተባባሪዎች በተገኙበት ግምገማው የተካሄደ ሲሆን ‘’ዓመተ-ጥራትን’’ በስኬት ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ጅምሮች መኖራቸውን የዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ጸክሉ ገልጸዋል።
ወ/ሮ ጸዳለ እንደገለጹት በዝግጅት ምዕራፍ የዘርፉን ዕቅድ ማስተዋወቅና የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸው ከጋራ መግባባት ወደትግበራ መገባቱን ገልጸዋል።
ይህ ሩብ ዓመት በአመዛኙ የዝግጅት ምዕራፍ ቢሆንም በርካታ ውጤቶች የተገኙበት መሆኑንም አብራርተዋል።
ኢንስቲትዩቱ ዓመቱን የጥራት ዓመት ብሎ መጀመሩን የገለጹት ም/ዋና ዳይረክተሯ ጥራትን ከቴክኖሎጂ ዘርፍ አንጻር ቃኝቶ መስራት እንደተጀመረ ገልጸዋል። ለዚህም የሠው የሀይል ዝግጁነት፣ የፈጠራ ችሎታ እየተፈተሸ እየዳበረ መሄድ ይገባል ብለዋል።
የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ከተቋም እሳቤ በላይ የአገራችንን የቴክኖሎጂ ፍላጎት የመመለስ ተልዕኮ ያለው በመሆኑ ከዚህ አንጻር መቃኘት እንደሚገባም ገልጸው በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የታየው መነሳሳት አበረታች ነው ብለዋል።
በዚሁ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከውጭ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎች የሚተኩ መፈጠር መቻላቸው አንዱ ስኬት መሆኑን አንስተው ነባር ቴክኖሎጂዎች ወደተጠቃሚው መድረስ የታሉበት መሆኑን ገልጸዋል።
ለዘርፉ የተለያዩ የአሰራር-ሰነዶች ዝግጅትና ትግበራ በሩብ ዓመቱ መሰራቱንም አብራርተዋል።
የክህሎት-ኢትዮጰያ ተሳታፊዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እንዲወዳደሩና ስራዎቻቸውም እንዲያስተዋውቁ የተመቻቸውን ትልቅ ስራ አንስተው ተሳታፊዎችም በውድድሮች ማሸነፍ መቻላቸው አገራችንን በዓለም መድረክ ማስተዋወቅ መቻላቸው በሩብ ዓመቱ ከተመዘገቡ ቁልፍ ስኬቶች መካከል ተጠቅሷል።
በቴክኖሎጂ ልማት፣ በኢንዱስትሪ ትስስር፣ በስቴም የስልጠና ማዕከል፣ በቴክኖሎጂ እንኩቤሽን ማዕከል፣ በቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ፣ በሃዋሳ ካምፓስ የቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በቴክኖሎጂ ማምራትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል የቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በስልጠና ፋከልቲዎችና በሌሎችም የዘርፉ ስራዎች የተከናወኑ ስራዎች በሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በየሥራ ክፍሉ መኖር ካሉባቸው ሰራተኞች በብዛት ያለመሟላታቸውና የበጀት ወስንነት መኖሩም ከየስራ ክፍሎች በቀረቡ ሪፖርቶችና በውይይት ላይ ተነስቷል።
ባሳለፍነው ዓመት የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎች ጥራትንና ፍጥነትን በማከል እየተሰሩ መሆናቸውን ወ/ሮ ጸዳለ ገልጸዋል።
የደንበኞቻችን አዳዲስ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ ስልጠናና ምርት ትርፍና ጥቅምን በሚያረጋግጥ ሁኔታ መሰራት አለበት ብለዋል።
የስልጠና ክፍሎች ከቴክኖሎጂና ከኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ጋር በይበልጥ በመቀናጀት ውጥታማ ስልጠናና ምርት በማስፋት ጥራትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ም/ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ አሳስበዋል።
May be an image of one or more people and text that says 'np FDRE የኢዜ INING TECHNICAL ስልጠና AETECHNICAL ጠና TECHNICAL& INSTITUTE ኢ ኢን & VOC'
May be an image of dais and text that says 'FDRE AINING ININHNICAL "ሐጠና DRE ከልጠና NINGNICAL& ጠና የኢባ AININGI ITUTE INSTITUTE VOCA &'
May be an image of one or more people and people studying