ኢንስቲትዩቱ ከአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ። **********ሰኔ 25/2017*******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ወርቁ ጋቸና ጋር በትብብር ለመስራት መክረዋል።
ዶ/ር ብሩክ፣ የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአገራችን በለውጥ ውስጥ ተወልዶ ትልቅ ኩራት የሆነ ተቋም መሆኑን አንስተዋል።
በአገራችን የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ መስኮች ስልጠናዎችን ለመስጠት የተዘጋጀው የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የገበያውን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ስልጠና የሚሰጠው መስኮች መለየቱን አንስተዋል።
በተለይም በሦስት የስልገና ዘርፎች ማለትም AI and Machin learning፣ AI and Robotics፣ cyber security ላይ ስርዓተ ስልጠና ዝግጅት በጋራ እንዲወጋጅ ጠይዋል።
የሁለቱ ኢንስቲትዩቶች ትብብር በተለይም የሰለጠነ የሰው ሀይል ማፍራት ላይ እና በዘርፉ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ፈጠራ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው ተቋማቸው በዘርፉ በርካታ አገልግሎቶችን ለአገር እያበረከተ መሆኑን በመግለጫቸው አንስተዋል።
የመረጃ ማጠናቀርን፣ ለትራፊክ እና ወንጀል ቁጥጥር
በጤናው ዘርፍ በተለይም የጡት ካንሰርን መከላከል የሚልችል ሲስተም ዘርግተዋል። በግብርናው ዘርፍ እና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር መስራታቸው በAI ዘርፉ ሙያተኞችን ማፍራት እና ቴክኖሎጂዎችን ማበልጸግ ሥራ ትልቅ አቅም እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።