የኢንስቲትዩቱ የመውጫ ፈተና በ10 ማዕከላት በመሰጠት ላይ ይገኛል። **********ሰኔ12/2017*******

የኢፌዲሪ ቴክኒክናሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች ላይ ተዘዋውረው የመውጫ ፈተና አሰጣጡን ተመልክተዋል።
የመውጫ ፈተና ዝግጅትና አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር ዓለሙ ኦሶሬ (ዶ/ር) እንደገለጹት 2ሺህ455 ሰልጣኞች በ10 ማዕከላት ፈተና እየወሰዱ ነው ብለዋል።
በፈተናውም በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና 15ሳተላይት ተቋማት ሰልጣኞችን ጨምሮ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ካርመንመንት ፋካሊቲ የክረምት ተማሪዎች 23 ትምህርት ክፍሎች ውስጥ በ46 ፕሮግራሞች እየተካፈሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።