የኢንስቲትዩቱ ሴኔት የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ። *****ሰኔ11/ 2017 ዓ.ም*****

የኢንስቲትዩቱ ሴኔት የ2017 ዓ.ም የስልጠና ጊዜ በሚመረቁ ሰልጣኞች ጉዳይና በኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ መምህራን የደረጃ ዕድገት ጉዳይ ተወያይቶ ወሳኔ ሰጥቷል።
ከኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢና የሳተላይት ካምፓሶች፣ በቅድመ-ምረቃና እና በድህረ-ምረቃ መርሀ- ግብር የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ስልጠናቸውን በስኬት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች እንዲመረቁ ሰኔቱ ወስኗል።
በውሳኔው መሰረት ከ1ሺ ሀምሳ በላይ ሰልጣኞች በሁለቱ መርሃ-ግብሮች በስልጠና ዓመታት ማሟላት በሚጠብቅባቸውን ብቃት፣ ክህሎትና አመለካካት አሟልተው ተገኝተዋል።
ሰልጣኞቹ በቀን፣ በማታ እና በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራሞች ስልጠናቸውን የተከታተሉ ሲሆን ሰኔ 15/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ በሚዘጋጀው ደማቅ ስነስርዓት ይመረቃሉ።
በተያያዘም ሰኔቱ በኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ መምህራን የደረጃ ዕድገት ረቂቅ መመሪያ ላይ የተወያየ ሲሆን፣ ተጨማሪ ግብዓቶችን አክሎ እንዲዳብር እና ለመጨረሻ ውሳኔ እንዲጠናቀቅ ለአርቃቂው ቡድን መርቷል።