ጥራት ማረጋገጥ ዓላማው ያደረገው የኢንስቲትዩቱ “ፋካሊቲ ቱር” በአግሮ ፕሮሰሲንግ ፋካሊቲ ተካሄደ። ********ግንቦት7/2017******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ተልዕኮዎቹን በጥራት ለመፈጸም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ለጥራት የሚያግዝ በየፋካሊቲዎች ያሉ ተግባራትን በመገምገም መፍትሄ የሚያስቀምጥ ፋካሊቲ ቱር እየተካሄደ ይገኛል።
ሁለተኛ ሳምንት ፕሮግራም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ፋካሊቲ ሲካሄድ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ ቱር ዓላማው እያንዳንዱ ፋካሊቲና ትምህርት ክፍሎችን ክትልል በማድረግ፣ በመገምገም ያለባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ፣ ለሌሎች ፋካሊቲዎች ልምድ ማለዋወ ነው ብለዋል።
በኢንስቲትዩቱ ጥራት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው የሁሉም አካላት ድርሻ ተደምሮ የሚመጣ በመሆኑ በየራሳቸው ለጥራት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ጥራት የሁሉም እና የሁልጊዜ ጉዳያችን ሊሆን ይገባል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ጥራት እንዲረጋገጥ፣ ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ሁላችንም ተግተን መስራት አለብን ብለዋል።
የፋካሊቲው ሀላፊ ዶ/ር ሳምራዊት ሙሉጌታ ሪፖርት አቅርበዋል። ሪፖርታቸውም ከስልጠና ጥራት፣ ጥናትናምርምር ላይ ካለ አበርክቶ፣በቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ ያለን ተሳትፎ የቃኘ ነው።
የተግባር ስልጠና ለማረጋገጥ ከኢንደስትሪው ጋር ያለው ትስስርም በውይይቱ ተዳስሷል።