ኢንስቲትዩቱ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ትብብር ለመፍጠር ያለመ ጉብኝት ተካሄደ። ******ሚያዚያ 17/2017******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እና ማኔጅመንት አባላት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጉብኝት አካሂደዋል።
ጉብኝቱ የተሰናዳው አብሮ ለመስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ እንደሆነ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ገልጸዋል።
ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚሊዮኖች ዜጎች የክህሎት ባለቤት የሚሆኑበት፣ ችግር ፈቺ ፈጠራዎች የሚወጡበት ዘርፍ ቢሆኑም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው አመለካከት የሚገባውን ያህል አይደለም ብለዋል።
ሁለቱ ተቋማት አብረው ቢሰሩ የኢንስቲትዩቱን ብቻ ሳይሆን የቴክኒክና ሙያ ገጽታ ለመገንባት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ም/ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ያስጎበኙ ሲሆን አብሮ ለመስራት የሚያስችል መነሻ ሰነድ አቅርበዋል።
በትብብሩ በሚሰሩ የሚዲያ ስራዎች ባለድርሻ አካላት ተከታታይነት ያላቸው ውይይቶችን እንዲያደርጉ እድል ይፈጥራል፤ ዜጎች ስለ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ያላቸው ግንዛቤ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በቀጣይ አብሮ መስራት የሚቻልባቸው ጉዳዮች ተዘርዝረው የስምምነት ፊርማ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል።





