“በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት የኢንስቲትዩቱን ዓመተ ልህቀት 2 ግቦች ለማሳካት የሚያስችሉ ሊሆኑ ይገባል” (ዶ/ር ብሩክ ከድር የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር) ******** ሚያዚያ 20/2017 ******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዓመተ-ልህቀት 2 ብሎ ሰይሞ እየሠራበት ባለው 2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት ውይይት መድረኩ የተዘጋጀው ባለፉት 9ወራት የተፈጸሙ ተግባራትን አፈጻጸም በመገምገም በቀሪ ወራት የተግባራት አፈጻጸም አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ የያዘው የማጽናት ዓመት ትልሞች እንዲሳኩ በሁሉም ዘርፍ ሁሉም አመራርና ሠራተኛ በትስስር መስራት እንደሚገባ ገልጸው የተገኙ ውጤቶችም በዚሁ አግባብ የተገኙ እንደሆነ ገልጸዋል።
ዶ/ር ብሩክ አያይዘውም በኢንስቲትዩቱ ያለውን የውስጥ አቅም አስተሳስሮ መጠቀም መቻሉ ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል። የኢንስቲትዩቱ ውጤት የሥራ ክፍሎች ተግባራት ተደምረው የሚመጣ ውጤት ነው ብለዋል።
የ9ወራት እቅድ አፈጻጸም በኢንስቲትዩቱ የአስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አዋቶ ቀርቧል።
በኢንስቲትዩቱ የተቀረጹ የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ብሩክ ከድር ቀርቧል።
የ9ወራት እቅድ አፈጻጸም በ4 ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ቀርቧል። እነሱም
1 ተቋማዊ አቅም ግንባታ
2 የስልጠና ጥራት፣ ተደራሽነትና አግባብነት
3 ጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት
4 ቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት
ከዚህም በተጨማሪ የሲቪልሰርቪስ ሪፎርም ላይ ትኩረት አድርጎ ቀርቧል።
በመድረኩ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ብሩክ ከድር ዓመተ-ልህቀት 2 እንዲሳካ በቀሪ ወራት በበለጠ በፍጥነት እና በበለጠ የመፈጸም አቅም መስራት የሚገባ መሆኑን ገልጸው ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አስቀምጠዋል።