የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የ9ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ። ********ሚያዚያ 14/2017******

የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ የዘርፉን የ9ወራት እቅድ አፈጻጸም ገምግመዋል።
በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በፖሊሲና ገበያ ጥናት መስኮች የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በሪፖርቱም ለ20ሳምንታት ሳይቆራረጥ የጥናትና ምርምር ሴሚናሮች መካሄዳቸው። በዚህም 36 የጥናት ውጤቶች ቀርበው ውይይት መካሄዱ ተገልጿል።
ከኢንስትቲትዩቱ አሰልጣኞች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ተመራማሪዎች እና የድህረምረቃ ሠልጣኞች ጥናታቸውን ማቅረባቸው ተገልጿል።
በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ተቋማትን ማጠናከር መቻሉ ሌላው በስኬት የተጠቀሰ ነው። የስልጠና ተቋማትን በገንዘብም በቁሳቁስም በመደገፍ ሰፊ ስራ ተሰርቷል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ ያለፉት 9ወራት በዘርፉ ትርጉም ያለው ስራ መሠራቱን ገልጸው ሊጠናከሩ ይገባቸዋል ያሏቸውን አንስተዋል።
ጥናትና ምርምር ሴሚናሮች በተጀመሩበት አግባብ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጠው በፋካሊቲ ደረጃ ሴሚናሮች ሊከናወኑ ይገባል ብለዋል።
የምርምር ፈንድ ማፈላለግ ክፍልም ተነቃቅቶ ትርጉም ያለው ስራ መስራት እንደሚገባ ዶ/ር ሀብታሙ ገልጸዋል።
በዘርፉ አዲስ የተቋቋመውን የፖሊሲና ገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በሙሉ አቅሙ ወደስራ እንዲገባ ይሰራል ብለዋል።
የባህል ልማት ዳይሬክቶሬትም የማደራጀት እና ወደስራ የማስገባት ስራ መሠራት እንዳለበትም ተናግረዋል።