የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሙያተኞች በፌደራል መንግስት የ9 ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ።
የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሙያተኞች በፌደራል መንግስት የ9 ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ።
********* ሚያዚያ 9/2017 *******
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ሁሉም አመራርና ሙያተኛ እንደአገር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የማወቅ፣ ለእቅድ ስኬትም የበኩሉን ድርሻ የማዋጣት ሀላፊነት አለብን ብለዋል።
እኛ እንደኢንስቲትዩት የምንሰራቸው ስራዎች እንደአገር በሁሉም ተቋማት የሚሰሩ ስራዎች ተደምረው ለአገራዊ ለውጥ ያግዛሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ በሁሉም ዘንድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መሰል ውይይቶች ያግዛሉ ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ የአስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አዋቶ ባለፉት 9ወራት በአገራችን የታቀዱ እና የተከናወኑ ተግባራትን የያዘ ሰነድ አቅርበዋል።
በሚለዋወጥ የአለም ኢኮኖሚ ውስጥ የአገራችን ኢኮኖሚ እንዳይናወጥ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፤ የተረጋጋ ማክሮኢኮኖሚ እና ምርታማነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተዳስሰዋል።
የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መስፋት በተሰራ ስራ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተገልጿል።
ቱሪዝም ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም እንዲሆን በተሰራ ስራ ትልቅ ሀብት መፍጠር መቻሉም ተብራርቷል።
ሠላምና መረጋጋት በአገር እንዲሰፍን መንግስት ያላሳለሰ ጥረት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።
See Translation





+11
All reactions:
Girma Teresa and 31 others